top of page

ህዳር 29፣ 2015የፔሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የቆዩት የ60 ዓመቷ ዲና ቦሉአርቴ የአገሪቱ ተጠባቂ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሐላ ፈፀሙ፡፡

ህዳር 29፣ 2015


የፔሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የቆዩት የ60 ዓመቷ ዲና ቦሉአርቴ የአገሪቱ ተጠባቂ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሐላ ፈፀሙ፡፡


ፕሬዝዳንት የነበሩት ፔድሮ ካስቲሎ በፓርላማው ተከስሰው ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡


አጋጣሚው ድራማዊ ሁኔታ አላጣውም ተብሏል፡፡


ፔድሮ ካስቲሎ ተከስሰው ከስልጣን ከመወገዳቸው አስቀድሞ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ፓርላማውን በትኘዋለሁ ብለው እንደነበር ተሰምቷል፡፡


ካስቲሎ በፓርላማው ተከስሰው ከስልጣን

መወገዳቸው ተከትሎ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የቆዩት ዲና ቦሉአርቴ ወዲያውኑ ቃለ መሐላ በመፈፀም የአገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ጊዜያዊ ርዕሰ ብሔር መሆናቸው ታውቋል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page