top of page

በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል ዛሬ በአቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተወነሰ፡፡

  • May 6
  • 1 min read

ሚያዝያ 28/2018


በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል ዛሬ በአቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተወነሰ፡፡


በተጠርጣሪዎቹ ላይ በአቃቤ ህግ ዛሬ የመሰረተባቸውን የክስ ዝርዝሩን ያደመጠው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል በስተቀር ሌሎቹ በዋስ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡


አቃቤ ህግ መንሱር ጀማልን በዋስትና እንዳይፈታ በመቃወሙ፣ መቃወሚያውን በፅሁፍ እንዲያስረዳ ችሎቱ ለመጪው ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


በዋስ እንዲለቀቁ ለተወሰነላቸው ተከሳሾችም በዋስትና የሚለቀቁበትን የገንዘብ መጠን ለመወሰን ፍርድ ቤቱ ለመጪው ሰኞ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


ተከሳሾች የ 1.9 ቢሊን ብር የማጭበርበር ጉዳት አድርሰዋል ያለው አቃቤ ሕግ ከደረሰው ጉዳት አንፃር የዋስትና ብሩ ከፍ እንዲልለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡


በተጨማሪም ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእሰር ቢለቀቁ እንኳን ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ እንዲጣልለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡


አቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የክስ ዝርዝር ዳንኤል ዩሃንስ ከተባለው ተከሳሽ እና ለጊዜው ካልተያዙ ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች መረጃን በማሰራጨት መግለፅ የሚገባቸውን መረጃ በመደበቅ የሶስተኛ ወገን ጥቅምን የሚጎዳ ድርጊት እንዲፈፀም ለማድረግ በማሰብ ስምምነት ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page