top of page

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የቀዳማይ ልጅነት ጉባኤ ልታሰናዳ ነው፡፡

  • May 6
  • 1 min read

ሚያዝያ 28/2018


ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የቀዳማይ ልጅነት ጉባኤ ልታሰናዳ ነው፡፡


ጉባኤው ለተማሪዎች ምገባ እና የትምህርት ቁስ ድጋፍ ለሚከነው ስራ የሚታዩ የፋይናንስ ችግሮችን ለመፍታት ያግዛል ተብሏል፡፡


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመው የቀዳማይ ልጅነት ማዕከል የልጆችን የተሟላ የጤና እንክብካቤ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ጥራት ያለው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መከታተል ዋና አላማው እንደሆነም ሰምተናል።


በዚህም 241 የመንግስት ትምህርት ቤቶች እና በ935 የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ላይ የምገባ ፕሮግራም፣ የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ እና የተማሪዎች ዩኒፎርም በነፃ በማቅረብ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነም እና ከ330,000 በላይ ተማሪዎች የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ ከበደ ወርቁ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡



በዚህም ኢትዮጵያ ከግንቦት 3 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በምታካሔደው ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባኤ ከሌሎች የአለም ሃገራት ጋር ትመካከራለች ተብሏል፡፡


ጉባኤው አፍሪካ በቀዳማዊ ልጅነት ሥርዓት ለውጥ የግንባር-ቀደምትነት ሚና ከአካባቢያዊ ሞዴሎች ወደ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ በሚል ይካሄዳል ተብሏል።


በጉባኤው ከሀገር ውስጥ፣ ከአፍሪካ፣ ከሌሎች የዓለም ሃገራት የተወጣጡ ከ350 በላይ ተሳታፊዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።


ይህ ጉባኤ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ የውይይት፣ የልምድና ዕውቀት ልውውጥእንዲሁም የመማማሪያ መድረክ ከመሆኑ ባሻገር የመፍትሄ ሀሳቦች እንደሚቀርቡበት ይጠበቃል ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 
በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡

ሰኔ 15/2018 በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት በተለያዩ ሶስት ፋብሪካዎች ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ ከ69 ቶን በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ

 
 
 

2 Comments


yaqian zhang
yaqian zhang
Jun 02

If you like physics-based driving challenges, Drive Mad is worth checking out. The balance between frustration and achievement feels just right.

Like

reginaldgoshim29034
May 08

To play Ragdoll Drop, I just drag and release the character to fall through different obstacles. The controls are simple, but timing and direction are very important.

Edited
Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page