top of page

70 በመቶ የሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች በአግባቡና በትክክል እጃቸውን እንደማይታጠቡ በጥናት ስለመረጋገጡ ተነግሯል።

  • 5 minutes ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 28/2018


70 በመቶ የሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች በአግባቡና በትክክል እጃቸውን እንደማይታጠቡ በጥናት ስለመረጋገጡ ተነግሯል።


ይህም የተላላፊ በሽታዎችን ተጋላጭነት በእጥፍ ይጨምረዋል ተብሏል።


ይህ የተባለው ዓለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀንን አስመልክቶ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ባሰናዳው መድረክ ላይ ነው።


በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልፀግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሄርጎ አበራ እጅን በአግባቡ መታጠብ በተላላፊ በሽታ የመሞትን ምጣኔ ከ18 በመቶ ወደ 2 በመቶ ይቀንሰዋል ብለዋል።


በኢትዮጵያ እጃቸውን በአግባቡ እና ሳይንሱን ተከትለው የሚታጠቡ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 30 በመቶ ብቻ መሆኑን ዶ/ር ሄርጎ አስረድተዋል።

ከታማሚዎች ፈሳሽ እና መሰል ነገሮች ጋር ንክኪ ያላቸው የጤና ባለሙያዎች ለተላላፊ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድላቸው 75 በመቶ በመሆኑ እጃቸውን ሳይንሱ በሚያዘው መልኩ መታጠብ አለባቸው ብለዋል።


እጅ መታጠብ የራሱ ቅደም ተከተል እና ሳይንሳዊ አካሄድ አለው ያሉት ዶ/ር ሄርጎ ብዙዎች ግን ይህንን እንደማይገነዘቡ አስረድተዋል።


በጤና ተቋማት፣ በምግብ ቤቶችና የሥራ ቦታዎች ንፁህ ውሃ፣ ሳሙናና የመታጠቢያ አልኮል በማቅረብ ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ የማበረታታት ልምድ ደካማ መሆኑንም ዶ/ር ሄርጎ አበራ አንስተዋል።

ብዙ ምግብ ቤቶች አንድ ሳሙና ለብዙ ሰው ያስቀምጣሉ፣ይህ የበሽታ አምጪ ጀርሞች መከማቻ እንጂ የንፅህና መጠበቂያ መንገድ እንዳልሆነም አስረድተዋል።


በዓለም የጤና ድርጅት ከ2009 ጀምሮ የእጅ መታጠብ ቀን ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን በጤና ሚንስትር የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ጤና ሚንስትር ከሌሎች ተቋማት ተጠሪዎች በተገኙበት በፖናል ውይይት ተከብሯል።


እጅን መታጠብ በንክኪ፣ በአየርና በፈሳሽ ተላላፊ በሽታዎችን 50 በመቶ፣ መድሃኒት የተላመዱ በሽታዎችን ደግሞ 70 በመቶ ይቀንሳልና እጃችሁን በየጊዜው በአግባቡ ታጠቡ ተብላችኋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል ዛሬ በአቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተወነሰ፡፡

ሚያዝያ 28/2018 በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል ዛሬ በአቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተወነሰ፡፡ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በአቃቤ ህግ ዛሬ የመሰረተባቸውን የክስ ዝርዝሩን ያደመጠው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል በስተቀር

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page