ህዳር 1 2018 - በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መታየት የነበረባቸው አዎንታዊ ለውጦች ለምን መታየት አልቻሉም?
- sheger1021fm
- Nov 10, 2025
- 1 min read
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ የዋለው ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ነው፡፡
ይህን ተከትሎም ከመስከረም በኋላ የብር የመግዛት አቅም ይጠናከራል የውጪ ምንዛሪ ግኝቱ ከፍ ይላል የሚሉ እና ሌሎችም የተጠበቁ ለውጦች ነበሩ፡፡
መሬት ላይ ሲታይ ግን በተቃራኒ ሆነው የተገኙም አሉ፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው?
የብር የመግዛት አቅም መጠናከር ሲኖርበት ከዕለት ዕለት አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እያሽቆለቆለ መሆኑን በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሞያ ጠቅሰዋል፡፡
ለዚህም አንደኛው ምክንያት የውጪ ምንዛሪ ገበያው ላይ ያለው ችግር መሆኑን አንስተዋል፡፡
የውጪ ምንዛሪውን ገበያ ከሚያውኩት መካከል የባንኮች አሰራር ግልፅ አለመሆን፣ የጥቁር ገበያው ጠንካራ ሆኖ መቀጠልና ሌሎችም ይገኙበታል ብለዋል፡፡
በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መታየት የነበረባቸው፤ አዎንታዊ ለውጦች ለምን መታየት አልቻሉም?
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments