ሁለተኛው ግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮጀክት በነገው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ተናገረ
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ህዳር 8 2018
ሁለተኛው ግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮጀክት በነገው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
ስራውን ለመተግበርም 128 ሚልዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡
የመጀመሪያው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ስራ ላለፉት 6 ዓመት ሲተገበር ነበር የተባለ ሲሆን 102 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡
በ2012 ዓ.ም በ600,000 ሄክታር መሬት ወደ ስራ ያስገባው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር 4.4 ሚልየን ገበሬ በክላስተር ተደራጅቶ የቴክኖሎጂና የተሻለ ግብዓት ተጠቃሚ ለማድረግ እንደተሰራ ሰምተናል፡፡
ባለፉት 6 ዓመታት በተሰራው ስራ 12 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በክላስተር እየታረሰ ነው ያሉት በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ዋና ዳይሬክተሩ ዳኛቸው ሌሉ(ዶ/ር) ናቸው፡፡
ከዚህ ባለፈም በክላስተር ሲታረስ ምርት ለመሰብሰብ የተሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም እና የምርት ብክነትን ለማስቀረት ይረዳል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የ2ኛ ዙር የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ግብርና ስራ 6.5 ሚሊዮን ገበሬን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡
ከያዝነው 2018 እስከ 2022 ድረስ ይተገበራል ለተባለው 2ተኛው ምዕራፍ 128 ሚሊየን ዶላር ለስራው ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
እስካሁንም ድረስ ከረጂ ተቋማት 66 ከመቶ የሚሆነው በጀት ተገኝቷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








