የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምዕራብ አፍሪካ ለምግብነት እየተላከ መሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎችን እና ጥሬ እቃ አቅራቢዎቻቸውን እያወዛገበ ነው፡፡
- 6 days ago
- 2 min read
ሚያዝያ 9/2018
የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምዕራብ አፍሪካ ለምግብነት እየተላከ መሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎችን እና ጥሬ እቃ አቅራቢዎቻቸውን እያወዛገበ ነው፡፡
ቆዳ አቅራቢዎቹ ያለምንም ልፋት በጥሬው ቆዳውን ለምግብነት ለሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት መላካቸው ፋብሪካዎቹን ጥሬ እቃ እያሳጣ ነው ተብሏል፡፡
መንግስት ቆዳ በጥሬው ለውጪ ገበያ የሚያቀርቡትን ለመግታት በበሬ ቆዳ ላይ የ150 በመቶ የታክስ ጭማሪ ስራ ላይ አውያለሁ ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ ለምግብነት አገልግሎት ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የመላክ አዝማሚያ መጨመሩን የኢትዮጵያ የቆዳ አምራቾች ማህበር ተናግሮ ነበር፡፡
ምርቱ በዋናነት የሚላከው ወደ ቶጎ እና ናይጄሪያ እንደሆነም ማህበሩ አመልክቷል፡፡
ይህን ተከትሎ የቆዳ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ምርታቸውን ለቆዳ ፋብሪካዎች ከማቅረብ ይልቅ፣ ለምግብነት ወደ ውጭ መላክን የበለጠ አትራፊ ስላደረጉት፣ በአገር ውስጥ በሚገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች የጥሬ ዕቃ እጥረት አስከትሏልም ብሏል፡፡

መንግስት የቆዳ ኢንዱስትሪን ለማበረታታት ጥሬ ወደ ሀገራቱ በሚላክ የበሬ ቆዳ ላይ 150 በመቶ የታክስ ጭማሪ ጥሎ እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡፡
አቅራቢዎች ግን የቆዳ ቆሻሻን ለማስወገድ በሚል ወደ ምዕራብ አፍሪካ መላካቸው ነው የተነገረው።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ፤ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ምርምርና ልማት ማዕከል በዚሁ ዙሪያ ጥናት አካሂዶ ውጤቱን ተጠሪ ለሆነለት መስሪያ ቤት ማቅረቡን ነግሮናል፡፡
አቶ ታረቀኝ ጂዳ በማዕከሉ የቆዳ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡
ጥሬ ቆዳ እርሰ በርስ የመጣበቅ ባህሪ ያለው ነው ያሉን አቶ ታረቀኝ ፤ ይህም በነጠላ ከፍተኛ ዋጋ ቢባልም ያን ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ለምግብነት ተብሎ ወደ ሀገራቱ የሚላከው የበሬ ቆዳ እሴት ተጨምሮበት ቢሸጥ የተሻለ ገቢ እንደሚገኝ የነገሩን አቶ ታረቀኝ ጉዳዩ ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋርም ተያይዞ ሊታይ ይገባዋል ብለዋል፡፡
አንድ የቆዳ ፋብሪካ ለብዙ ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል የሚሉት አቶ ታረቀኝ ፤ ተቀጣሪዎቹ በስራቸው ሌሎች ብዙ ቤተሰቦች ሊኖራቸው እንደሚችል አክለዋል፡፡
እነዚህ ፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ አጥተው ስራ አቆሙ ማለት የእነዚህ ሁኑ ሰዎች ኑሮ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ነው የጠቀሱት፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





In Buckshot Roulette, I hesitate because the situation feels too balanced to trust. That uncertainty makes the moment intense.