top of page

በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

  • Apr 23
  • 1 min read

ሚያዝያ 15/2018


በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።


ይህንን ፕሮጀክት ይፋ ያደረገው ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ሲሆን ፕሮጀክቱ ለ6 ወር እንደሚቆይ እና 4.5 ሚሊዮን ዶላር እንደተመደበለትም ሰምተናል።



የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር አንበሱ ቶላ (ዶ/ር) እንዳሉት ይህ ባለብዙ ዘርፍ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጀክት በጤና፣ በሥርዓተ-ምግብ እና በንፁህ መጠጥ ውሃ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ ነግረውናል።


የ4.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት ፕሮጀክቱ ለዚህም በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ፈንድ (EHF) ድጋፍ አድርጓል።


የፕሮጀክቱ ዋና ግብ በኦሮሚያ ክልል 5 ዞኖች በተመረጡ 7 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 295 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ፤ በችግር ምክንያት የሚከሰቱ የህመም እና የሞት መጠኖችን ፈጣን ምላሽ በመስጠት መቀነስ ነው ተብሏል።


ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ከ24 ዓመታት በላይ የተቸገሩ ሰዎቸን ሲያግዝ የቆየ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ነው።


በዛሬው ዕለት 17ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን እያደረገ ይገኛል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……



ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 
በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡

ሰኔ 15/2018 በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት በተለያዩ ሶስት ፋብሪካዎች ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ ከ69 ቶን በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page