top of page

የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶችን ሲሸጡ የተገኙ 44 የመድሃኒት መደብሮች ተቀጡ፡፡

  • sheger1021fm
  • 3 hours ago
  • 1 min read

ጥር 22/2018

 

የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶችን ሲሸጡ የተገኙ 44 የመድሃኒት መደብሮች ተቀጡ፡፡

 

በመደሮቹ ላይ እስከ እገዳ የደረሰ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

 

ባለስልጣኑ በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ በመድሃኒት መሸጫ መደብሮች ከወንኩት ባለው የቁጥጥር ስራ 1275 ኪሎ ግራም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች ማግኘቱንና ግምታዊ ዋጋቸውም 5.5 ሚሊዮን ብር መሆኑን የነገሩን በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገልገሎ ኦልጅራ ናቸው፡፡

 

መድሃኒቶቹ መወገዳቸውን የተናገሩት ሃላፊው ይህንን ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት ይዘው የተገኙ 44 የመድሃኒት ችርቻሮ መደብሮችና 2 የባህል ህክምና ባለሙያዎች ላይ ከከባድ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የሙያ ፍቃድን የማገድ እርምጃ ስለመወሰዱም አስረድተዋል፡፡

 

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 112 ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ የጤና ተቋማት አንድን ህክምና ለመስጠት በሚያስችላቸው ቁመና ላይ ባለመገኘታቸው ከደረጃ በታች በሚል በባለስልጣኑ ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ገሚሶቹ ሲሰጣቸው ገሚሶቹ ደግሞ የሙያ ፍቃዳቸው ታግዷል ተብሏል፡፡

 

በተጨማሪም ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ 778  አዲስ የህክምና ሙያ ብቃት ወስደው ወደ ስራው ገብተዋል፤በተመሳሳይ ለ1ሺህ 628 የመድሃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች አዲስ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው ወደ ስራው ስለመግባታቸው ሰምተናል፡፡

 

በስራ ላይ ያሉትም በየ3 ዓመቱ ፍቃዳቸውን ማደሳቸውን እንደሚከታተል የጠቀሱት ሃላፊው ያለ ሙያዊ ፍቃድ እንዳይሰራ እንዲሁም የሚሰጠውም አገልግሎት ከተቀመጠው ደረጃ በታች እንዳይሆን ማድረግ ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

 

በቁጥጥር ስራው የሚሰጡት ህክምና አገልግሎት ከደረጃ በታች ነው የተባሉ 112 የጤና ተቋማትን ጨምሮ ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት ሲሸጡ ነበር የተባሉት 44 የመድሃኒት መደብሮችና 2 የባህል ህክምና ባለሙያዎች ባጠቃላይ በ1መቶ 58 ግለሰቦችና ተቋማት ላይ እርምጃው መወሰዱን ሰምተናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ምንታምር ፀጋው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page