top of page

ታህሳስ 8፣ 2015- ፀሐይ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ለማሳደግ ዛሬ በአንደኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መወሰኑ ተሰማ


ፀሐይ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ለማሳደግ ዛሬ በአንደኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መወሰኑ ተሰማ፡፡


የባንኩ ካፒታል 2 ቢሊየን 162 ሚሊየን 534 ሺህ ብር በመጀመር ወደ 5 ቢሊየን ብር እንዲያድግ ተወስኗል፡፡


ይህም የገንዘብ መጠን እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር 2024 ድረስ ተከፍሎ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ባንኮች ሊኖራቸው የሚገባው ዝቅተኛ የካፒታል መጠን ላይ ማሻሻያ በመደረጉ እና ይሄንኑ ማሻሻያ በተገቢው መልኩ ማሟላት አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡


የፀሐይ ባንክ ካፒታል አቅሙን በመጨመር ከሌሎች ባንኮች ጋርም ተወዳዳሪ ለማድረግ እንዲቻል እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡


የውጪ ባንኮች በአገር ቤት ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቀድ ፖሊሲ በመውጣቱ በባንኮች ላይ በሚፈጠረው ውድድር አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ፀሐይ ባንክ የተሻለ የካፒታል ቁመና ላይ መገኘት አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡


ፀሐይ ባንክ የተፈረመ ካፒታል 2 ቢሊየን 837 ሚሊየን 466 ሺህ ብር ነው፡፡


የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 865 ሚሊየን 976,500 ብር ነው፡፡


ተህቦ ንጉሴ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page