በቤት ሰራኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች መብታቸውን እና ግዴታቸውን አውቀው እንዲሰሩ የሚያደርግ ህግ ሊወጣ ነው፡፡
በህጉ መሰረት ከ15 ዓመት በታች የሆኑትን መቅጠር በህግ ያስቀጣል፡፡
በአንድ በኩል የቤት ሰራተኞቹ በአሰሪዎቻቸው ሲበደሉ እና ጥቃት ሲደርስባቸው ይታያል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እራሳቸው ተቀጣሪዎቹ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ ይስተዋላል፡፡
በአሰሪ እና ሰራተኛ መሀል ያለን ክፍተት ለመድፈንም ይረዳል የተባለ የህግ ማዕቀፍ በቅርቡ ተግበራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም #የአሰሪ_እና_ሰራተኛ አዋጁ ላይ የቤት ሰራተኞች ባለመካተታቸው በስራ ሂደት ውስጥ ከሚያጋጥሟቸው ወንጀሎች በስተቀር ሌሎች መብቶቻው ሲጣሱ የሚጠይቁበት ህግ እነዳልነበረ ሰምተናል፡፡
ይህንን የሰማነው የአዲስ አበባ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዚሁ ዙሪያ ከሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመከረበት ወቅት ነው፡፡
የቤት ሰራተኞች መብታቸውን እና ግዴታቸውን አውቀው እንዲሰሩ የሚያርግ የህግ ማዕቀፍ አለመኖሩ አካላዊ ድብደባ፣ ከፍተኛ የስራ ጫና፣ ፆታዊ ጥቃት እና መሰል ጥቃቶች ሲፈፀሙባቸው ይስተዋላል ይላሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ህግ ስርፀት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አቃቤ ህግ ወይዘሪት ህዳት ጌታቸው፡፡

የቤት ሰራተኞችን መብት ለማስጠበቅ ለአምስት ዓመታት ስራዎችን እየከወንኩ ነው የሚለው አንድነት ኢትዮጵያ #የቤት_ሰራተኞች ህብረት የቤት ሰራተኞችን የሚመለከት ህግም እንዲወጣ ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ተናግሯል፡፡
በዚህም በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል የሚሉት የህብረቱ ፕሬዚደንት ሂሩት አበራ ህጉ ተግባራዊ መሆን ሲጀምርም ከዚህ ቀደም ሰራተኞችም ሆኑ አሰሪዎች ሲያጋጥሟቸው የቆዩ ችግሮቻቸው ይቀንሳሉ ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ይናገራሉ፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የመቀጠሪያ እድሜ ነው 15 ዓመት ቢሆንም ግን ከ10 ዓመት እድሜ በታች የሆኑትም #ህፃናት ተቀጥረው እንደሚሰሩ የሚናገሩት የህብረቱ ፕሬዝደንት ህጉ ወደ ትግበራ ሲገባም ከ15 ዓመት በታች ቀጥሮ የተገኘን ሰው ተጠያቂ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ህጉ ወደ ተግባር ሲገባ ለቀጣሪዎች ያለው ጥቅም ምንድን ነው ስንል የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ህግ ስርፀት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አቃቤ ህግ ወይዘሪት ህዳት ጌታቸው ይህንን ብለውናል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments