የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች የግሽበት ግብር ስለመኖሩ ይናገራሉ፡፡
ይህም እስከ 35 በመቶ ከደመወዙ ላይ የስራ ግብር የሚቆረጥበትን ደመወዝተኛ ግሽበቱ ሌላ ተጨማሪ 35 በመቶውን ያሳጣዋል እንደማለት ነወ፡፡
ለዚህም ነው ወር ጠብቆ ደመወዝ ለሚያገኝ ተቀጣሪ የዋጋ ግሽበት አብዝቶ የሚፈትነው ይላሉ ባለሞያዎች፡፡
በዚህ ረገድ የደመወዝተኛውን ችግር ለማቃለል ደመወዝ ከመጨመር ይልቅ የተጋነነ የሚባለው የገቢ ግብሩን መቀነስ የተሻለ አማራጭ ነው ተብሎ ፤ መንግስት የተቀጣሪውን የገቢ ግብር እንዲቀንስ እየተጠየቀ ነው፡፡
በሌላ በኩል አነስተኛ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ 5 ሊትር ዘይት ለመግዛት የማያስችል ወርሃዊ ደሞዝ ያላቸው ብዙዎች ኑሮ ዳገት ሆኖባቸዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ምን እየተሰራ ነው?
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments