top of page

መጋቢት 26፣2016 - ኢትዮጵያ የህዝቧን ቁጥር ሊስተካከል የተቃረበ ያህል በግ እና ፍየል እንዳላት ይነገራል

ኢትዮጵያ የህዝቧን ቁጥር ሊስተካከል የተቃረበ ያህል በግ እና ፍየል እንዳላት ይነገራል፡፡


ሀገሪቱ 90 ሚሊዮን በግ እና ፍየል እንዳላት ሲነገር ቢሰማም ለአብዛኛው ሰው ግን ስጋ ለዓመት በዓልም ቢሆን ብርቁ ነው፡፡


ዋጋውም የሚቀመስ አልሆነም፡፡


የኢትዮጵያ በግ እና ፍየሎች በየድንበሩ እየተነዱ የኮንትሮባንድ ሲሳይ መሆናቸውም አልቀረም፡፡


የበግ እና ፍየል ስጋ ብርቅ እንዳይሆን በማሰብ የተለያዩ ሀገር ዝርያዎችን ወደ ሀገር ቤት በማምጣት፣ ለማዳቀል የተደረገው ጥረትም እንደታሰበው አልሆነም፡፡


የበግ እና ፍየል ስጋ ብርቅ እንዳይሆን፣ ተሽጠውም ዶላር እንዳያመጡ፣ እርባታውም አካባቢን እንዳይጎዳ ለማድረግ ያለመ ፕሮጀክት ባለፉት 15 ዓመታት ሲሞከር መቆየቱን ሰምተናል፡፡


ፕሮግራሙ ''ማህበረሰብ አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ'' እንደሚባል ሰምተናል፡፡


ከሌላ ሀገር ዝርያ ማምጣት ሳያስፈልግ እዚሁ ሀገር ቤት ካሉት የተሻሉትን ዝርያዎች በማዳቀል የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ተነግሯል፡፡


ፕሮጄክቱ በ 200 መንደሮች ተግባራዊ ተደርጎ ውጤቱም ጥሩ መሆኑን በአለም አቀፉ ድርቃማ አካባቢዎች የግብርና ምርምር (Icarda) ውስጥ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ለሸገር ተናግረዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1


Comments


bottom of page