ጥቅምት 11 2018 - በኢትዮጵያ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን በተለያየ መልኩ እየረዳ መሆኑን የአለም ምግብ ድርጅት ተናገረ።
- sheger1021fm
- 4 hours ago
- 1 min read
የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሙቲንታ አምባይ(ዶ/ር) ይህንን ያሉት ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተከበረው የአለም የምግብ ቀን ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
ምርጥ ዘር እና ግብዓት በማቅረብ፣ የማጨጃ እና መውቂያ መሳሪያዎችን በመለገስ፣ በገንዘብ ድጋፍ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር እና በሰብል እና እንስሳት ኢንሹራንስ በሀገሪቱ ከ1.5 ሚሊየን በላይ አርሶ፣ አርብቶ እና ከፊል አርሶ አደሮችን እየደገፈ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ካለፈው ጥር ጀምሮ ወደ 47,000 አርሶ አደሮች 35,000 ሄክታር በ5 ክልሎች እየለማ መሆኑን የተናገሩት የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ከዚህ ውስጥ ከ10,000 በላይ የሚሆነው በመስኖ እየለማ ነው ብለዋል።

ምርታማነትን ማሳደግ፣ ገቢን በመጨመር ማህበረሰቡን ከጥገኝነት የማውጣት ስራ ከመንግስት እና ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንም የአለም የምግብ ድርጅት ተናግሯል።
የአለም የምግብ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ማህበረሰብ መር የሆነ መፍሔዎችን እንደሚደግፍ የተናገሩት የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሙቲንታ አምባይ(ዶ/ር) ይህም ዘላቂ የውሃ አቅርቦትን እንዲኖር፣ የሃብት ግጭቶችን ለመቀነስ እና እንስሳትን ለመጠቀም እንደሚረዳ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ የምግብ ደህንነት የሚረጋገጠው አነስተኛ አርሶ አደሮች፣ ሴቶች እና ወጣቶች እኩል የሃብት፣ የእርሻ እና የገበያ እድል ሲያገኙ እንደሆነ ድርጅቱ ጠቀሟል።
የአለም የምግብ ድርጅት ምግብ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰዎች፣ በፈጠራ፣ በአካታችነት እና በአዲስ ትውልድ ላይ መዋለ ንዋይ እያፈሰስኩ ነው ሲል ተናግሯል።
ከግብርና በላይ የአለም የምግብ ድርጅት ከ14,000 በላይ ተጋለጭ የሆኑ ሴቶችን፣ ህፃናትን ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ምግብ እንዲያገኙ እያደረግሁ ነው ብሏል።
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ወደ 280,000 ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን በትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ መድረግ መቻሉን ጠቁሟል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s