መስከረም 27 2018 - የባንኮች የብድር ጣሪያ ገደብ
- sheger1021fm
- Oct 7
- 1 min read
ባንኮች ለኢኮኖሚው የሚያበደሩት ወይም በብድር መልክ ወደ ገበያው የሚለቅቁት ገንዘብ ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር እድገት በያዝነው ወር ሙሉ በሙሉ ይነሳል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይነሳ ቀርቷል፡፡
የብድር እድገት ጣርያ ከነበረበት 18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡
የፋይናንስ ባለሞያው አቶ ጥላሁን ግርማ አሁን ገብያው ባለበት ሁኔታ ከፍተኛ ብድር ወደ ገብያ መልቀቅ የዋጋ ንረቱ እንዲባባስ ምክንያት ሊሆን ይችላል ይላሉ፡፡
የብሄራዊ ባንክ አካሄድ ጥንቃቄ የተሞላበት እንደሆነ የሚያስረዱት አቶ ጥላሁን የብድር እድገት ጣርያው ገደብ አለመነሳቱ ተቀዛቅዘው የሚገኙትን አንዳንድ የስራ መስኮች በዚያው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
ለማሳያም የሪል ስቴት እና የመኪናው ገበያ መዳከሙን ያስረዱት አቶ ጥላሁን ግርማ ይህም የገንዘብ አቅርቦት መጥፋቱን ያሳያል ብለዋል፡፡
የዋጋ ንረቱን የማያባብስ እና ኢኮኖሚውን የማይጎዳ መላ መዘየድ አስፈላጊ እንደሆነ የሚናገሩት ባለሞያው የብድር ጣሪያውን ገደብ ለሁሉም መስክ ተመሳሳይ ማድረግ ለኢትዮጵያ አስፈላጊ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ፡፡
ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገባው እና በሀገር ውስጥ ለሚያመርተው እኩል የብድር ስርዓት መኖር እንደሌለበት የሚያስረዱት የፋይናንስ በለሙያው አቶ ጥላሁን ግርማ፤ ምክንያቱ ደግሞ ከውጭ ምርቶችን የሚያስገቡት የዋጋ ንረቱ የሚያባብስ ሲሆን በሀገር ውስጥ የሚመረተው ደግሞ የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍተኛ ድርሻ ስላለው ነው ብለዋል፡፡
ሌላው የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረ-ዮሃንስ በበኩላቸው የብድር እድገት ጣሪያው ላይ የተደረገው መሻሻያ በቂ ባይሆንም ገብያውን በተወሰነም ቢሆን ለማነቃቃት እንደሚረዳ አስረድተዋል፡፡
ይህ ጣርያ ከሶስት ወራት በኋላ ሙሉ በሙሉ ይነሳል ብለው እንደሚጠብቁ የሚናገሩት አቶ መርዕድ ምክንያታቸውንም አስረድተዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments