የመካከለኛ ምስራቅ ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ እጥረት አምራች ፋብሪካዎች ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡
- 1 hour ago
- 2 min read
መጋቢት 25/2018
የመካከለኛ ምስራቅ ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ እጥረት አምራች ፋብሪካዎች ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡
የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ፋብሪካዎች በነዳጅ እጥረት ምክንያት ጥሬ እቃ ተወዶብናል ፣ ተፅዕኖዎቹን ተቋቁመን የምርት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ኢራን ከአሜሪካና እስራኤል ጋር እያካሄደችው ያለው ጦርነት በእኛም ሀገር እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖውን እያሳረፈ ነው።
የትራንስፖርት ዘርፉ ተጠቃሽ ሲሆን አሁን ያለውን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የነዳጅ ግብይት መከተል እንደሚገባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሠሞኑ ማሳሰቡ ይታወሳል።
የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ተከትሎ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መስተጓጎል እንዳይፈጠር ፤
መንግስት ነዳጅን ከተጓዳኝ ገበያ በሶስት እጥፍ ዋጋ እየገዛ ለማቅረብ መገደዱን ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው።
የጦርነቱ ተፅዕኖ የተለያዩ ምርቶችን በሚያወጡ ፋብሪካዎች ላይ እየታየ ስለመሆኑማወቅ ችለናል
ተፅዕኖው በጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ፤ በትራንስፖርት ዋጋ መጨመር እና በነዳጅ እጥረት እንደሚገለጽ ከፋብሪካዎቹ የስራ ሃላፊዎች ሠምተናል።
ፈሳሽ ሳሙና የሚያመርተው የዘመኑ ታከለ እና ጓደኞቹ ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ኃ/ማርያም እንደነገሩን የጥሬ ዕቃ ዋጋ ከጦርነቱ በኋላ በጣም እየጨመረባቸው ነው።
በዚህም ምክንያት የምርት ሂደቱን ጋብ ለማድረግ ተገደናል ብለውናል።
የቦኤዝ የምግብ ኮምፕሌክስ ባለቤት ዮሴፍ ታደሰ በበኩላቸው ነዳጅ በስራቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረባቸው እንደሚገኝ ነው የነገሩን።
የነዳጅ እጥረቱ ከቀጠ የምርት ሂደታችንን ሊጎዳው ይችላል የሚል ስጋት አለን የኒው ዊንግ አዲስ ጫማና ቆዳ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ኢቫኖ መስፍን ደግሞ ጦርነቱን ተከትሎ ከቻይና የምናስገባው ጥሬ ዕቃ ዋጋ በእጥፍ ጨምሮብናል ብለዋል።
ምርቱን ለማጓጓዝ ይጠየቅ የነበረው የትራንስፖርት ዋጋም እንዲሁ በእጥፍ መጨመሩን ነው የነገሩን።
ኒው ዊንግ አዲስ ጫማና ቆዳ ፋብሪካ ምርቶቹን የሚልከው ወደ አሜሪካ ገበያ እንደሆነ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ኢቫኖ መስፍን ፤ኢትዮጵያ ከአጎዋ መታገዷን ተከትሎ የተጣለው ታሪፍም ሌላው ተፅዕኖ ሆኖብናል ብለዋል።
አሜሪካ ከሰሀራ በስተደቡብ ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ከሰጠችው የቀረጥ እና ኮታ ነጻ ዕድል ኢትዮጵያ መታገዷን ተከትሎ አስር በመቶ ታሪፍ ለመክፈል መገደዳቸውን ጠቅሰዋል።
የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ደግሞ ተጨማሪ አስራ አምስት በመቶ ታሪፍ መጣሉን በማስታወስ አሁን ላይ በአጠቃላይ ሃያ እምስት በመቶ ታሪፍ እየከፈለን ነው ብለዋል።
ተፅዕኖዎቹ ቢኖሩም የምርት ሂደታቸው እንዳይስተጓጎል ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የፋብሪካዎቹ የስራ ሃላፊዎች ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments