የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ የጭነት መኪኖች ምልልስ በመቀነሱ የወጪ ንግዱ የሚላክበት ኮንቴይነር እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡
- 1 hour ago
- 1 min read
መጋቢት 25/2018
በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ የጭነት መኪኖች ምልልስ በመቀነሱ የወጪ ንግዱ የሚላክበት ኮንቴይነር እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡
በጅቡቲ የባዶ ኮንቴይነሮች ክምችት ቢጨምርም መኪኖች ወደ ሀገር ቤት በበቂ ሁኔታ ሊያመጧቸው ስላልቻሉ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ባዶ ኮንቴነሮችን ወደ ሀገር እያስገባ እንደሚገኝ ነግሮናል።
የኢትዮ ጁቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት የቢዝነስ ደቨሎፕመንት እና የማርኬቲንግ ክፍል ሃላፊ ኤደን ተስፋዬ በተለይ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ለተሰማሩ ድርጅቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ላኪዎች ከድርጅቱ ጋር እንዲሰሩ እና በተፈጠረው ችግር ምክንያት መስተጓጎል እንዳይኖር እንዳያደርጉም ሃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።
ድርጅቱ ለወጪ ንግዱ ቅድሚያ በመስጠት ጭነቶችን ለማመላለስ ዝግጅት እንደጨረሰም ተሰምቷል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments