top of page

ተማሪዎች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት (AI) አጠቃቀም ላይ ከመምህራኖቻቸው ቀድመው የሚገኙ ከሆነ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ክፍተት መፍጠሩ አንደማይቀር ተጠቆመ።

  • 3 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 12 2018


ተማሪዎች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት (AI) አጠቃቀም ላይ ከመምህራኖቻቸው ቀድመው የሚገኙ ከሆነ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ክፍተት መፍጠሩ አንደማይቀር ተጠቆመ።


ችግሩን ለመቅረፍ መምህራንን በቴክኖሎጂው ማብቃትና AIን በራሱ እንደ አንድ የትምህርት ኮርስ አዋህዶ መስጠት እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ተመራማሪዎች አሳስበዋል።


ሰው ሰራሽ አስተውህሎት እያሳየ ባለው እድገት ምክንያት ከጊዜ በኋላ መምህራንን ሊተካ ይችላል የሚል ስጋትን ደቅኗል ተባለ፡፡


በኮተቤ የትምህርት ዩንቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አበበ አለሙ መምህራኑ በአግባቡ ለዚህ ቴክኖሎጂ ማዘጋጀት ከተቻለ ጊዜያቸውን እንዲጠቀሙ ተማሪዎቻቸውንም እንዲያበቁ ይረዳቸዋል ይላሉ፡፡


ይህ ካልሆነ ግን ቴክኖሎጂው እየሄደበት ባለው ፍጥነት ያልበቃውን መምህር ሊተካ ይችላል ፣ ተማሪዎችም መምህሩን እንዲበልጡት ሊያደርግ ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን ነግረውናል፡፡


ሌላኛዋ በሰው ሰራስ አስተውህሎት ዘርፍ ተመራማሪ የሆኑት ሰርካለም ንጉሴ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ጥቅም ላይ ሲውል ጥንቃቄን ይፈልጋል ብለዋል፡፡


ተማሪዎች ከዚህ ቴክኖሎጂ ጋር ያላቸው ቅርበት ከመምህራኑ የቀደመ ሆኖ ይገኛል ያሉት ተመራማሪዋ መምህራን ስልጠና ሲሰጣቸው ይህን ቴክኖሎጂ እንዴት ረዳት አድርገው እንደሚጠቀሙት ማስተማር ይገባልም ሲሉ አስረድተዋል፡፡



ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....



በረከት አካሉ





Recent Posts

See All
የነሐሴ 12 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሩሲያ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ብሪታንያን በብርቱ አስጠነቀቋት፡፡ ፑቲን ብሪታንያ ለዩክሬይን ግዛት ተሻጋሪ ድሮኖችን ከማቀበል ብትቆጠቢ ይሻልሻል ማለታቸው ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ቀደም ሲል ታይምስ ጋዜጣ ዩክሬይን በሩሲያ ላይ ግዛት ተሻጋሪ ጥቃት የምታደርሰው በብሪታንያ ስሪት ድሮኖች እንደሆነ መዘገቡ ተጠቅሷ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page