top of page

የክልሎች ህገ መንግስት በክልሉ ያሉ ሁሉንም ብሔሮችን በሚጠብቅ መልኩ እንዲሻሻል እና "ልዩ ሃይል" አፍርሰናል ያሉ ክልሎች በገለልተኛ አካል ኦዲት እንዲደረጉ በተቋማት ግንባታ ስር ሲመክር የቆየው ቡድን ያለ ልዩነት መስማማቱ ተነገረ።

  • 1 hour ago
  • 2 min read

ነሐሴ 13 2018


የክልሎች ህገ መንግስት በክልሉ ያሉ ሁሉንም ብሔሮችን በሚጠብቅ መልኩ እንዲሻሻል እና "ልዩ ሃይል" አፍርሰናል ያሉ ክልሎች በገለልተኛ አካል ኦዲት እንዲደረጉ በተቋማት ግንባታ ስር ሲመክር የቆየው ቡድን ያለ ልዩነት መስማማቱ ተነገረ።


በተቋማት ግንባታ ስር ሲመክር የቆየው ቡድን "ልዩ ሃይል" አንዲፈርስ ፣የክልል ፖሊስም በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ ሆኖ በሚዘጋጅ የስልጣን ሰነድ እንዲሰለጥን ከስምምነት መድረሳቸውን ሸገር ከቡድኑ አባላት ሰምቷል።


ክልሎች የሚኖሯቸው የሚሊሻ አባላትም በወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠኑ ይሁኑ በሚለው መመሪያ ላይ የተስማማው ቡድኑ አንድም የክልል የጸጥታ አደረጃጀት የመከላከያ እና ፌደራል ፖሊስን የሚገዳደር ሃይል እንዳይኖረው በሚለው መስማማታቸውን ተመካካሪዎች ነግረውናል ።


ተመካካሪው ብድን ክልሎች አፍርሰናል ያሉት "ልዩ ሃይል " በገልተኛ ወገን ኦዲት እንዲደረግ ተስማምተናል ብለዋል።


ተመካካሪዎች ገለልተኛ ቡደን የተባለው አካል ሲጠቅሱ ደግሞ መከላከያ እና የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ለማሳየት ዘርዝረዋል ።


ሌላው ይህ ቡድን መከርኩበት እና ተስማማሁበት ያለው በክልሎች ለንጽሃን መፈናቅል "ምክንያት "ናቸው ያላቸውን የክልሎች ህገ መንግስትን የተመለከተ ነው።


በዚህ የአንዳንድ ክልሎች ህገመንግስት ዜጎች ያለ ክልላቸው ሃብት ጥበቃ አይደርግም ይህም ለንጽሁን መፈናቅል ምክንያት ሆኗል ።


ሰለዚህ ለክልሉ ብሔሮች ብቻ ሃብት እንዲፈሩ የሚፍቅዱ የክልል ህገ መንግስቶች እንዲሻሻሉ ተጠይቋል።


አንዚህ ምክረ ሀሳቦች የመጨረሻ ለመሆነ ነገ በጉባዔተኞች መጽደቅ ይኖርበታል ።


በሌላ በኳል በለፉት ቀናት በተመረጡ 34 አጠናቃሪዎች እርስ በእርስ እንዳይጋጩ ሲጣጣሙ የቆዩ አጀንዳዎች ዛሬ ለ500 ቡድን አባላት ይቀርባሉ።


ቡድንም ተጣጥመው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ የመጨረሻ ግብዓት ሰጥቶ በሳምቱ መጨረሻ 4ሺውም ጉባዔተኛ ለአጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦችን ያጽድቃል ተብሎ ይጠበቃል።



እስካሁን ባለው ሂደት ለአጀንዳዎች የቀረቡ ወይንም የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች በሁሉም ባይሆንም በተወሰኑት ከአንድ በላይ ናቸው።


እንዚህም ምክረ ሀሳቦች ወደ አንደ እንዲጠቡ የምክክር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ስላሴ ለ4ሺ ተመካካሪዎች ትናንት ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል ።




ምክትል ኮሚሽነሯ እዚህ የመጣውን ለመስማማት ስለሆ ምክረ ሀሳቦችን ወደ አንድ ማጥበብ አለብን ብለዋል።


አዲስ አበባ ላይ ሲመክር የቆየው ብድንን ጨምሮ ከፍተኛ ክርክር እና ልዪነት ያለባቸው ምክር ሀሳቦች እንዴት ወደ አንድ ምክረ ሀሳብ ይሰበሰባል የሚለው የሚጠበቅ ይሆናል።


ያሬድ እንዳሻው

Recent Posts

See All
አስፈጻሚው የመንግስት አካል በግለሰቦች ላይ በደል ሲፈፅም የሚቀጣበት የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ስራ ላይ ቢሆንም ብዙዎች ነገሬ ብለው እንደማይጠቀሙበት በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎች ነግረውናል፡፡

ነሐሴ 13 2018 አስፈጻሚው የመንግስት አካል በግለሰቦች ላይ በደል ሲፈፅም የሚቀጣበት የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ስራ ላይ ቢሆንም ብዙዎች ነገሬ ብለው እንደማይጠቀሙበት በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎች ነግረውናል፡፡ አዋጁን የማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው የፍትህ ሚኒስቴር ይህንን ጉዳይ ለመዳኘት በፌድራል ፍ

 
 
 
ተማሪዎች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት (AI) አጠቃቀም ላይ ከመምህራኖቻቸው ቀድመው የሚገኙ ከሆነ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ክፍተት መፍጠሩ አንደማይቀር ተጠቆመ።

ነሐሴ 12 2018 ተማሪዎች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት (AI) አጠቃቀም ላይ ከመምህራኖቻቸው ቀድመው የሚገኙ ከሆነ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ክፍተት መፍጠሩ አንደማይቀር ተጠቆመ። ችግሩን ለመቅረፍ መምህራንን በቴክኖሎጂው ማብቃትና AIን በራሱ እንደ አንድ የትምህርት ኮርስ አዋህዶ መስጠት እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ተመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page