ትምህርት ሚኒስቴር ባስገነባቸው 9 ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶች ተማሪዎችን ፈትኖ ለመቀበል መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ነሐሴ 13 2018
ትምህርት ሚኒስቴር ባስገነባቸው 9 ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶች ተማሪዎችን ፈትኖ ለመቀበል መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

ባለፈው አመት በ5 ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶች 1ሺ 250 ተማሪዎች ተቀብሎ እያስተማረ እንደነበር የጠቀሰው ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 4 ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ብሏል፡፡
ባህር ዳር ፣ አርባ ምንጭ ፣ ድሬዳዋ እና አሶሳ አዳዲስ ልዩ ኣዳሪ ትምህርትቤቶች ሲሆኑ ቡኢ ፣ ወሊሶ ፣ጅግጅጋ ፣ ጋምቤላ እና ቦንጋ ደግሞ ነባሮቹ የፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡
ዘንድሮ ወደ ፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርትቤት ለመወዳደር የ8ተኛ ክፍል ውጤታቸው 80 ከመቶና ከዛ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ኬጥኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመወዳደር ብቁ ናቸው ተብሏል፡፡
ከጠረፍ እና አርብቶ አደር ከሆኑ አካባቢዎች የሚመጡ ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ውጤታቸው ዝቅ ቢልም በልዩ ሁኔታ ሊታዩ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡
በሁሉም ክልሎች ቢያንስ አንድ ልዩ አዳሪ ትምህርትቤት ለመክፈት ትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ ነው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
በረከት አካሉ
_edited.jpg)


Comments