ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ነሐሴ 6 2018
ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡
ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል ተብሏል፡፡
በጨረታው 28 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው የድርሻቸውን ተጫርተው የወሰዱ ባንኮች ቁጥር 9 መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ለጨረታው የቀረበው ከፍተኛው ገንዘብ 163 ብር ከ98 ሳንቲም ሲሆን ዝቅተኛው 159 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፡፡
ዛሬ ይፋ በሆነው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር መቅረቡን ይፋ ያደረገው ብሔራዊ ባንክ ቀጣዩን የጨረታ ጊዜም በፕሮግራሙ መሰረት ይፋ አደርጋለው ብሏል፡፡
ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ ላይ የቀረበው የውጭ ምንዛሬ መጠን 125 ሚሊየን ዶላር ቢሆንም በባንኮቹ በኩል የቀረበው ፍላጎት ግን 470.17 ሚሊየን ዶላር መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
ቴዎድሮስ ወርቁ
_edited.jpg)



Comments