top of page
ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡
#ታሪክን_የኋሊት ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ መነኮሳቱና ዲያቆናቱ እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጠው ጀኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ነበር፡፡ ጀኔራል ግራዚያኒ የኢጣሊያ የምስራቅ ዕዝ አዛዥና በኋላም የኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ገዥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መነኮሳት ላይ የተለየ ጥላቻ ነበረው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ ኢትዮጵያ እንዳትገዛልን የሚያወግዙ፣ ስለነፃነት የሚሰብኩ፣ አርበኞችን የሚደግፉ ናቸው ፤ የሚል እምነት ስለነበረው ቤተ ክርስቲያኗን ለመበተን ይመኝ ነበር፡፡ የካቲት 12፣ አብርሃም ደቦጭ በቦምብ ካቆሰለው በኋላ ፣ሚስቱን ደብረ ሊባኖስ ገዳም መደበቁን ሰማ፡፡ ይኽም በካህናት መ
5 days ago2 min read


‘’የበጋው መብረቅ’’ ሌተና ጀነራል ጃገማ ኬሎ
#ታሪክን_የኋሊት ‘’የበጋው መብረቅ’’ በሚል ቅፅል ስማቸው የሚታወቁት ሌተና ጀነራል ጃገማ ኬሎ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በ2009 ዓ.ም በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡ አርበኛው ጃገማ ኬሎ ጣሊያን ኢትዮጵያ በወረረችበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረጋቸው ይታወቃሉ፡፡ ጃጋማ ኬሎ የተወለዱት በጅባትና ሜጫ አውራጃ በደንቢ ዮብዲ ወረዳ ውስጥ በ1913 ዓ.ም ነው፡፡ ጃገማ ለቤተሰቦቻቸው የመጨረሻ ልጅ ናቸው፡፡ በልጅነታቸው ወላጅ አባታቸውን በሞት በማጣታቸው ያደጉት ከአጎታቸው ጋር ነው፡፡ አደን ይወዱ የነበሩት ጃገማ የ15 ዓመት ወጣት እያሉ ጣሊያን ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ ታዳጊው አዳኝ ከሌሎች የኢትዮጵያ አርበኞቸ ጋር ሆነው ጫካ ገቡ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ አርበኞችን በማስተባበር ታዋቂ የጦር መሪና አስተባባሪ መሆን ቻሉ፡፡ በተለያዩ የጦር ሜዳዎች የኢጣሊያ
Apr 72 min read


ታሪክን የኋሊት -የማይጨው ጦርነት
#ታሪክን_የኋሊት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የማይጨው ጦርነት የተደረገው በ1928 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ኢጣሊያ በሊቢያና በሱማሊያ ከኢትዮጵያ ክፍል ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት ይዛ ከቆየች በኋላ፣ ጠቅላላ ኢትዮጵያን በሃይል ለመውረር ጦርነት ከፈተች፡፡ በምፅዋ ወደብ ፣ በኤርትራ በኩል ወደወሰን ዘመናዊ የጦር ሃይሏን አደራጀች፡፡ የወልወልን ግጭት ሆን ብላ ከቀሰቀሰች በኋላ፣ ተበዳይ ሆና ለመቅረብ ሞከረች፡፡ አከታትላም ዋናው የጦር ሃይሏን ባደራጀችባት ኤርትራ በኩል፣ ወሰን ጥሳ፣ በጥቅምት ወር መቀሌን ያዘች፡፡ ከወራሪው የኢጣሊያ ሃይል ጋር ሲወዳዳር፣ ኋላ ቀርና አነስተኛ መሣሪያ ያለው አብዛኛው፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የክተት አዋጁን ተከትሎ፣ ስንቁን ይዞ፣ ጦርና ጋሻውን አንግቦ ወደዘመቻው ተሰማራ፡፡ ኢጣሊያ፣ በሶማሊያ በኩል ባደራጀችው ዘመናዊ የ
Mar 312 min read


በኢትዮጵያ የዛሬ 51 ዓመት በዛሬው ቀን የገጠር መሬት አዋጅ ታወጀ፡፡
#ታሪክን_የኋሊት በኢትዮጵያ የዛሬ 51 ዓመት በዛሬው ቀን የገጠር መሬት አዋጅ ታወጀ፡፡ የካቲት 25 ቀን 1967 የወጣው የመሬት አዋጅ ከዚያ በፊት ሰፍኖ የቆየውን የመሬት አጠቃቀምና ስሪት ለውጦ ከባለርስቱ ወደ አራሹ ገበሬ ያዛወረ አዋጅ ነበር፡፡ የመሬትን ባለቤትነት ላራሹ የማድረግ አስፈላጊነት ጥያቄ በጊዜው ለነበረው ንጉሳዊ መንግስት ከተለያዩ ክፍሎች ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ገበሬዎች በሰላማዊና በአመፅ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡ የጊዜው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በተደራጀ መልኩ በአመፅ ጥያቄውን ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የመሬት ስሪት ፣ በርስትነት በገባርነት የሚያዝ ሆኖ ቆይቷል፡፡ መሬት በአብዛኛው ትውልድ ቆጥሮ ወይም በውርስ የሚይዙት ፣ ሲሆንም ነባሩን ነዋሪ አፈናቅሎ በአገልግሎትና በስጦታ የሚሰጥ ይዞታ ነበረው፡፡ በአገልግሎትና በስጦታ በሰ
Mar 42 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

