top of page

ሰኔ 16/2018 - የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ሂደት እስካሁን አለመጀመሩ እንዳሳሰበው ኢሰመኮ ተናገረ፡፡

  • 1 hour ago
  • 1 min read

ሰኔ 16/2018


የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ሂደት እስካሁን አለመጀመሩ እነዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡


ኮሚሽኑ የተዘጋጁት ረቂቅ ሕጎችና ሰነዶችም ለሕዝብ ውይይት እስከ አሁን አለመቅረባቸው ያሳስበኛል ብለዋል።


ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው ዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የ11 ወራት አቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ለህዘብ እንደራሴዎች ምክርቤት ባቀረበበት ሰነዱ ላይ ነው፡፡


በሚያዝያ 2016 ዓ.ም የጸደቀው የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ፍኖተ ካርታ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉን ያስታወሰው ኮሚሽኑ በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የተመላከቱትን ዋና ዋና ተቋማት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆች መቀረጻቸው ጠቅሰዋል፡፡



ፖሊሲውን ለማስፈጸም መሰረት የሆነው የዓለም አቀፍ ወንጀሎች ሕግ ከሽግግር ፍትሕ ሂደት መጠናቀቅ በኋላም በዘላቂነት ተግባራዊ ሊደረግ በሚችልበት አግባብ መረቀቁ ተገቢ መሆኑን አስረድቷል፡፡


በሽግግር ፍትሕ ሂደት የተጎጂዎችንና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ የሚመራ ረቂቅ ስትራቴጂ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን አክሏል፡፡


ይሁንና በሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ ካርታው መሠረት ሊተገበሩ የሚገባቸው የሽግግር ፍትሕ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር መድረክ ማቋቋም ፣የትግበራ ቅደም-ተከተል ጥቅል ዕቅድ ማውጣት፣የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን፣የሕዝብን እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን ድጋፍና የባለቤትነት ስሜት የሚያጠናክሩ ሥራዎችን የማከናወን ተግባሩ በታቀደለት ጊዜ አለመፈጸሙ አሳሳቢ ነው ብሏል ኮሚሽኑ፡፡


የተዘጋጁት ረቂቅ ሕጎችና ሰነዶችም ለሕዝብ ውይይት እስከ አሁን አለመቅረባቸው የሚሳስብ ጉዳይ እንደሆነ አስረድቷል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page