ጥቅምት 4 2018የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን እንድታቋቁም የሚያስችላትን ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አጸደቀ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 14
- 1 min read

ሀገሪቱ የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤና አገልግሎት፣ በሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ላይ ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት የመምራትና የማስተባበር ሃላፊነት እንዲኖረው ተደርጎ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል ተብሏል፡፡
ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ ከተወያየበት በኋላ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትረ ጽ/ቤጽ ተናግሯል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሌለው የተወያየበት ጉዳይ በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በወጣ ደንብ ላይ ነው፡፡
ተቋሙ የሚሰጣቸውን የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የተግባር ተኮር ስልጠናና ማማከር እና የስፔሻላይዝድ ላባራቶሪ አገልግሎቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ በማቅረብ ወጪውን በሙሉ ሸፍኖ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ እንዲችል የአገልግሎት ክፍያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይከተወያየበት በኋላ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ተብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments