ጥቅምት 3 2018 - የመምህርነት ሞያ ያላቸው ታራሚዎች እና የፖሊስ አባላት ተመልምለው፤ እዚያው ባሉ ት/ቤቶች እንዲያስተምሩ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 13
- 1 min read
በማረሚያ ቤት የሚገኙ የመምህርነት ሞያ ያላቸው ታራሚዎች እና የፖሊስ አባላት ተመልምለው፤ እዚያው ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲያስተምሩ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
ባለሞያዎቹ ያገለገሉበት ሰዓትና ቀን ተቆጥሮ ክፍያ እንደሚፈፀምላቸውም ከፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሰምተናል፡፡
ከመምህራን በተጨማሪ በተለያየ የሞያ ዘርፍ ያሉና ልምድ ያላቸው ታሚዎች በተለያየ ዘርፍ ስራ እየሰሩ ገቢም እያገኙ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ይህንን የነገሩን በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና መሪ ስራ አስፈፃሚ አስመራ አብደታ ናቸው፡፡

በተለይ በማረሚያ ማዕከላት በሚገኙ የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ተቋማት የሚያገለግሉ ታራሚዎች ጥቂት አይደሉም ተብሏል፡፡
በምህንድስና፣ በግብርና፣ በጋርመንት ስራ እና በሌሎች ሞያዎች እውቀት እና ልምድ ያላቸው ታራሚዎች በቴክኒክና ስልጠና ተቋማቱ ስልጠና እንደሚሰጡ አቶ አስመራ አስረድተዋል፡፡
በቤተ-መፅሀፍት ውስጥ የሚያደለግሉ እና ጎልማሶችን የሚያስጠኑ አጫጭር ስልጠናዎች የሚሰጡ እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ማረሚያ ተቋማት ት/ቤቶች፤ ከያሉበት ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች መምህራን እንደሚመድቡ ሰምተናል፡፡
ማረሚያ ቤቶች የሚቀጥሯቸው መምንህራን ትምህርት ቢዎሮዎች ከሚመድቡላቸው መምህራን ተጨማሪ እና ወጪያቸውም በማረሚያ ተቋማቱ የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በፌደራል ማረሚያ ማዕከላት የሚገኙ 5 ት/ቤቶች ውስጥ 1,300 ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ ከሀላፊው ሰምተናል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ስር ያሉ ታራሚ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማሳለፍ ምጣኔ ከሀገራዊ የማሳለፍ ምጣኔ ከእጥፍ በላይ ነው መባሉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments