top of page

ጥቅምት 28፣2016 የስራ ኢንተርፕራይዞች በኤሌክትሮኒክስ መላ መገበያያት የሚያስችል መተግበሪያ ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ


በኢትዮጵያየሚገኙ የስራ ኢንተርፕራይዞች ያመረቱትን ምርት በቀላሉ በኤሌክትሮኒክስ መላ መገበያያት የሚያስችል መተግበሪያ ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ።


የስራእና ክህሎት ሚኒስቴር ለተለያዩ አላማዎች የሚውሉ ሶስት መተግበሪያዎችን ወደ ስራ ማስገባቱ ተነግሯል።


ሚንስቴርመስሪያቤቱ ያለማቸው 3 መተግበርያዎች የኢንተርፕራይዞች ኤሌክትሮኒክስ መገበያያ (ሉሲ)፣ የቴክኒክና ሞያ ስልጠና መመዘኛ (COC)እና የስራ ማግኛ መተግበሪያዎች ናቸው ተብሏል።


የስራእና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈርያት ካሚል የሉሲ መተግበሪያ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ ያመረቱትን ምርት በኤሌክትሮኒክስ መገበያያት የሚያስችል ነው ብለዋል።


ከዚህበፊት የነበረው የሲኦሲ ምዘና ስርዓት ሙሉ ለሙሉ ባይባልም ለሀሰተኛ ማስረጃ መስፋፋት አንዱ ምክንያት ነበር ተብሏል።


ይህንምለማስቀረት አዲሱ መተግበሪያ ወጥ የሆነ ፈተና ለመስጠትና የሙያ ተቋማት መረጃ ለማወቅ ያግዛል መባሉን ሰምተናል፡፡


የሲኦሲመተግበሪያው ብቁ እና አቅም ያለው ባለሞያ ለመፍጠር ይረዳል ሲሉ ወይዘሮ ሙፈርያት ተናግረዋል።


በሌላበኩል ብቁ የተሰኝው መተግበሪያ ወጣቶች ስራዎችን በዲጂታል መንገድ የሚያፈልጉበት እና ማግኘት የሚችሉበት አሰራር መሆኑን ተነግሯል።


ይህአሰራር በሀገሪቱ ያለውን የስራ አጥ ቁጥር በቀላሉ ለማወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡

በረከት አካሉ


የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page