top of page

ጥቅምት 21 2018 - ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው?

  • sheger1021fm
  • 5 hours ago
  • 1 min read

ከ3 ዓመታት ወዲህ የሚታየው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ላይ ያሳደረው የስነ ልቦና ጫና ተስፋ እስከመቁረጥ የደረሰባቸው መሆኑን ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተማሪው፣ በትምህርት ባለሞያው እንዲሁም በተማሪ ቤተሰቦች ቅሬታ እያስነሳ ነው፡፡

 

ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው? ስንል በጠየቅንበት ወቅት ቤተሰብ ልጆቻቸው እንዲማሩላቸው ስለሚፈልጉ አልያም አልተማሩም ላለመባል ብቻ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡ 

 

ይህንን ሀሳብ የሰማነው ከዘንድሮ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ነው፡፡

 

ree

ተማሪዎቹ አሁን ላይ ለትምህርት ስላላቸው ፍላጎት እና እያስተናገዱት ስላለው ስሜት ምን ይጠቁመናል? ስንል ባለሞያ አነጋግረናል።

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እቅድ እና ስራ አመራር ትምህርት ክፍል ባልደረባ ደሞዜ ደገፋ(ዶ/ር) አሁን እየታየ ያለው የ12ተኛ ክፍል ውጤት መውረድ በትምህርት ላይ ያሉትን ተማሪዎች የመማር ፍላጎታቸው እንዲቀንስ እና ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋቸዋል ይላሉ። 

 

የፈተና ውጤቱ ችግር መኖሩን አሳይቷል የሚሉት  ደሞዜ(ዶ/ር) ተማሪው ይኮርጅ ነበር የሚለው ላይ ብቻ ከማተኮር በአግባቡ የሚማሩበት ሁኔታ አለ ወይ? ብቁ መምህራን አሉ ወይ? የሚለው መፈተሽ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 

ትምህርት በብቁ ሰዎች መመራት እንዳለበትና ተማሪዎችም ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት በደንብ መማራቸው መረጋገጥ አለበት ብለዋል፡፡

 

ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page