ጥቅምት 20 2018የኮተቤ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢን በክለዋል የተባሉ በገንዘብ ተቀጡ።
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዞችና የወንዞችን ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 1.6 ሚሊዮን ብር መቅጣቱን ተናግሯል።
በየካ ክፍለ ከተማ፣ 3 ተቋማት የከብት እርባታ ፍሳሽን ቀጥታ ወደ ወንዝ በመልቀቅ፣ 3ቱም ማህበራት እያንዳንዳቸው 300,000 ብር በድምሩ 900,000 ብር መቀጣታቸው ተነግሯል።
የኮተቤ ዩኒቨርሲቲም ከፍተኛ ብክለት በመፈፀሙ 400,000 ብር እንዲቀጣ መደረጉንም ተቋሙ ተናግሯል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ኢትዮ ቤስት ሪል ስቴት የተባለው ተቋምም ፈሳሽ ቆሻሻን ከወንዝ ጋር በማገናኘት ወንዞችንና ወንዝ ዳርቻዎችን መበከሉ ስተረጋገጠ 300,000 ብር ተቀጥቷል ተብሏል።
ወንዞችና የወንዞችን ዳርቻ ለታለመላቸው ልማት እዲውሉ የማድረግ ሀላፊነት አለብኝ ያለው ተቋሙ ህብረተሰቡ የደንብ መተላለፍ ሲያይ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ ይስጠኝ ብሏል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








