ጥቅምት 20 2018 - በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚበሩ መንገደኞች፤ የቲኬት ክፍያቸውን በቻፓ መፈፀም ይችላሉ ተባለ።
- sheger1021fm
- 5 hours ago
- 1 min read
ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ መካከል በዛሬው ዕለት ተፈርሟል።
በስምምነቱ መሰረት በየትኛውም የአለም ክፍል የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የበረራ ቲኬታቸውን በቻፓ የዲጂታል የክፍያ አቀላጣፊ መላ ተጠቅመው መፈፀም ይችላሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አዠ ባደረጉት ስምምነት የማንኛውንም ባንክ ኤቲ ኤም (ATM) ካርድ በበይነ መረብ ላይ በመጠቀም የበረራ ትኬትን መግዛት ያስችላል ተብሏል፡፡
በአየር መንገዱ በይነ መረብ እና የስልክ መተግበሪያ (mobile app) አማካኝነት የማንኛውንም ባንክ ኤቲ ኤም (ATM) ካርድ መለያ ቁጥርን በመጠቀም የበረራ ትኬትን መግዛት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋታቸዉን ተጠቅሷል፡፡
ስምምነቱ የበረራ ክፍያዎችን ለመፈጸም ቀላል፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ተብሎለታል።
"የአየር በረራን በፊንቴክ - Flight Meets Fintech" የሚል መሪ ቃልም ተሰጥቶታል፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆሊዴይ እና ዲጂታል ሽያጭ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሀይለመለኮት ማሞ እና የቻፓ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናኤል ኃይለማርያም ፈርመውታል።
የኢትዮጵያ የአር መንገድ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ከሌሎች የዲጂታል የክፍያ አቀላጣፊዎች ጋር አብሮ ለመስራት መስማማቱ ይታወሳል።
ከግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በክፍያ አቀላጣፊነት አብሮ ለመስራት የተፈራረመው ቻፓ እስካሁን ድረስ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያዎችን ማስተላለፋ ተጠቅሷል።








