top of page

ጥቅምት 20፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች


የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት(ሐማስ) ከ3 ሳምንታት በፊት ካገታቸው ሰዎች መካከል እንደሆኑ የተገመተን የ3 ሰዎች የቪዲዮ ምስል እዩልኝ አለ፡፡


በቪዲዮ ምስሉ ላይ አንደኛዋ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን በብርቱ ሲነቅፉ እንደሚሰማ CBS ፅፏል፡፡


ሴትዮዋ ሁላችንንም ታጋቾች አስለቅቃቸዋለሁ አልክ ግን የት አለ? ሲሉም ተጠምደዋል፡፡


ችግሩም የጦሩ እና የፖለቲካ አመራሩ ውድቀት ነው ሲሉ አክለዋል፡፡


የእስራኤል መንግስት ከሐማስ ጋር የእስረኞች ልውውጥ እንዲያደርግ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡


ሐማስ እስካሁን በሰብአዊ ርህራኔ ባለው ምክንያት ጥቂተ ታጋቾችን ብቻ ነው የለቀቀው፡፡


በእጁም ከ200 በላይ ታጋቾች እንደሚገኙ ሲነገር መሰንበቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡


ሐማስ እዩልኝ ባለው ቪዲዮ ድምፃቸው የሚሰማው ወይዘሮ አስተያየት በፈቃዳቸው ይሁን ተገድደው የታወቀ ነገር የለም፡፡


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን ሐማስ የቪዲዮ መልዕክቱን ማውጣቱን የጭካኔ ተግባር ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በጋዛ በጭራሽ ተኩስ አናቆምም አሉ፡፡


ኔታንያሁበጋዛ ተኩስ አናቆምም ያሉት ከየአቅጣጫው ተኩስ እንዲቆም ጥሪው በበረታበት ወቅት እንደሆነ KBC በድረ ገፁ ፅፏል፡፡


የእስራኤሉጠቅላይ ሚኒስትር ተኩስ ማቆምን ለሐማስ እጅ ከመስጠት እንቆጥረዋለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የእስራኤልጦር በጋዛ በስልታዊነት እየገፋ እንደሆነ ኔታንያሁ ተናግረዋል፡፡


ጦርነቱከተቀሰቀሰ አንስቶ የእስራኤል ጦር ጋዛን ያለ ማቋረጥ በአየር እና በሚሳየል መደብደብ መቀጠሉን ዘገባው አስታውሷል፡፡


የተባበሩትመንግስታት የረድኤት አካላት በጋዛ የሰላማዊ ፍልስጤማውያንን ስቃይ እና መከራ ለመቀነስ ተኩስ ተማፅኗቸውን እንዲቆም አላቋረጡም ተብሏል፡፡


ኔታንያሁግን ጊዜው የጦርነት ነው ፤ የተኩስ አቁም ብሎ ነገር አይኖርም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡



በናይጀርያበደረሰ የጀልባ ተገልብጦ መስጠም አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች መጥፋታቸው ተሰማ፡፡


አደጋየገጠማቸው መንገደኞች ከአካባቢያዊ የዓሣ ገበያ በመመለስ ላይ እንደነበሩ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


ተገልብጣየሰጠመችዋ ጀልባ ከ100 በላይ መንገደኞችን አሳፍራ ነበር ተብሏል፡፡


14 ሰዎችን በሕይወትማትረፍ ሲቻል የ17 ሰዎች አስከሬን መገኘቱ ታውቋል፡፡


አደጋውየደረሰው ታራባ በተባለችው ግዛት እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


ናይጀርያየጀልባ ተገልብጦ መስጠም አደጋ የሚደጋገምባት አገር እንደሆነች ዘገባው አስታውሷል፡፡



የአለምየሙቀት መጠን ጭማሪ በእጅጉ እየፈጠነ እንደሆነ የመስኩ የሳይንስ ሊቃውንት ተናገሩ፡፡


የሙቀትመጠን ጭማሪው ከቅድመ ኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ከነበረው ሲመሳከር ከ6 ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ ከ1.5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እንደሚልቅ ሊቃውንቱ ማስጠንቀቃቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ይሄምአስቀድሞ ሲገመት ከነበረው ጊዜ በእጅጉ የፈጠነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


እንደድንጋይ ከሰል እና የነዳጅ ዘይት ያሉ ብክለት አስከታዮችን ጥቅም ላይ ማዋሉ እየጨመረ መምጣቱ ለችግሩ ጉልህ ድርሻ አበርካች ነው ብለዋል ሊቃውንቱ፡፡


በዚህምየተነሳ ባለፉት 3 ዓመታት ወደ ከባቢ አየር የተለቀቀው የበካይ ጋዝ መጠን የምንግዜውም ከፍተኛው እንደነበር ሊቃውንቱ ለማስጠንቀቂያቸው በምሳሌነት ጠቅሰውታል፡፡


ከ8 አመታት በፊት በፓሪሱ የአየር ለውጥ ጉባኤ አገሮች የአለማችን የሙቀት መጠን ጭማሪ ከቅድመ ኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ሲመሳከር ከ1.5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እንዳይበልጥ ቃል ግተው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡


አለምወደ ኢንዱስትሪ አብዮት ከተሸጋገረች 170 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡


የኔነህከበደ


የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz


bottom of page