top of page

ጥቅምት 18 2018 - በቢሾፍቱ የሚገነባው አዲሱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከፍታ ምክንያት የነበሩ ችግሮችን የሚፈታ ነው ተባለ።

  • sheger1021fm
  • Oct 28
  • 1 min read

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በከፍታ ቦታ ላይ በመገኘቱ አውሮፕላኖች ብዙ ነዳጅ ጭነው ለመነሳት ይቸገሩ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

 

ይህም ለምሳሌ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ በሚደረግ በረራ በቂ ነዳጅ ይዞ መነሳት ስለማይችል ከቦሌ የሚነሳ አውሮፕላን ደብሊን ላይ አርፎና ነዳጅ ሞልቶ ለመነሳት ይገደዳል ብለዋል።

 

ree

በቢሾፍቱ የሚገነባው አዲሱ ኤርፖርት ግን ከቦሌ ዝቅ ባለ ከፍታ ላይ የሚገኝ ስለሆነ ይህንን ችግር ይፈታል ብለዋል።

 

ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ100 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል የተባለው አዲሱ ኤርፖርት ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ቀዳሚ ኤርፖርት ባለቤትም ያደርጋታል ብለዋል።

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page