top of page

ጥቅምት 18 2018 በመንግስት ልዩ ትዕዛዝ የተሰጡትን በሺዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን ሊያመርት መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • 6 hours ago
  • 2 min read

አስተዳደሩ ይህን የተናገረው የ3 ወር(የሩብ ዓመት) የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳይዎች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ጥር 17ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረቡበት ወቅት ነው።


የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄ በንባብ ያቀረቡት የምክር ቤት አባሉ አቶ ሳዲቅ አደም በሩብ ዓመቱ ተቋሙ ለማበልጸግ ከያዛቸው እቅዶች ውስጥ አንዱ #የድሮን_ቴክኖሎጂ መሆኑን አስታውሰው በ3 ወራት ውስጥ ተመርተዋል ስልተባሉ ድሮኖች ማብራሪያ ቢሰጥ? ሲሉ ጠይቀዋል።


የአስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በሰጡት ምላሽ የተቋሙ አንዱ ሃላፊንት በሀገራዊ አቅም ባልተሰራባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ መስራት መሆኑን አስረድተው ይህንንም ታሳቢ አድርገን በድሮን ቴክኖሎጂ ላይ ምርምር የማድረግ፣ የማበልጸግ፣ የመቆጣጠር እና አገልግሎት የመስጠት ስራ እየሰራን ነው ሱሉ ተናግረዋል።

ree

ይህን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ደግሞ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን አምና "ሰካይዩን" የድሮን ማምረቻ ዘንድሮ "ኤሮ አባይ "የተሰኘ የድሮን ማምረቻ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ሃላፊዎቹ አስረድተዋ ።


ባለፉት ሶስት ወራትም በእነዚህ የድሮን ማምረቻዎች ውስጥ 300 ድሮኖች መመረታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠቁሟል።


የድሮን ማምረቻዎቹ ለአንድ ወይም ለሁለት የድሮን አይንቶች ማምረቻ ብቻ የሚውሉ ሳይሆኑ ለወታደራዊ እና ሌላ አገልግሎት የሚውሉ ድሮኖችንም ያመርታሉ ተብሏል ።


አሁን በዋናነት እየተመረቱ ያሉት ድሮኖች ግን ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራትም አገልግሎት ላይ በመዋል ገቢ የሚያመጡ ናቸው ተብሏል።


ድሮኖችን የማምረት ሂደቱ አሁንም መቀጠሉን የተናገሩት የስራ ሃላፊዎቹ በህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ እና በኢሬቻ በዓል ላይ ለትርኢት አገልግሎት ላይ የዋሉትም በሀገሪቱ አቅም የተገጣጠሙ ናቸው ሲባል ሰምተናል።


ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመቅረጽ እና ለቁጥጥር የሚረዱ መቶ ድሮኖችም በአሁኑ ወቅት በምርት ሂደት ላይ መሆናቸው የተነገር ሲሆን በተጨማሪ ደግሞ በመንግስት በልዩ ሁኔታ እንዲመረቱ የተሰጡ ትዕዛዞች አሉ እንሱንም በሺዎች ለማምረት ጥሬ እቃ የማመቻቸት ስራ አስተዳደሩ እየሰራ ነው ተብሏል።


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፉት ሶስት ወራት 13443 የሳይበር ጥቃቶች፣ ሙከራዎች መፈጸማቸውን እና አምና በተመሳሳይ ወቅት የተፈጸመው የጥቃት መጠን ግን 6700 አካባቢ መሆኑን የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ አብራርተዋል።


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page