ጥቅምት 17 2018 - በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጽሑፍ ቅርሶች አስመዝጋቢ ኮሚቴ ሥራ ጀምሯል።
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ኮሚቴው የኢትዮጵያን አብያተ መዛግብት እና ታሪካዊ መጻሕፍትን በዩኔስኮ የዓለም የትውስታ ማህደር (Memory of the World) ላይ ያስመዘግባል ተብሏል።
ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት 12 የሚደርሱ ጥንታዊ ፅሑፍና መዛግብቶቿን የዓለም የትውስታ ማህደር ላይ አስመዝግባለች።
ይሁን እንጂ ሀገሪቷ ካላት ሰፊና የረጅም ዘመናት የሥነ ፅሑፍ ታሪክ አንፃር የተመዘገቡት ከቁጥር የሚገቡ አይደሉም ተብሏል።
ለዚህም ሲባል ኮሚቴ አቋቁሞ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተነግሯል።

ከአንድ ዓመት በፊት ተቋቁሞ የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ትምህርትና የባህል ማዕከል(UNSCO) ተወካይእና የቱሪዝም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ሥራ የጀመረው ኮሚቴው ሁለት ተጨማሪ መዛግብቶችን ለማስመዝገብ ተቃርቤያለሁ ብሏል።
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








