ጥቅምት 17 2018 - በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጠመ።
- sheger1021fm
- 4 hours ago
- 1 min read
የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ ነበርም ተብሏል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተሰማው ትናንት ጠዋት 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ(2:24)ላይ እንደነበረም ተነግሯል።
ይህንን የነገሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊቪክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና የአስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪ አታላይ አየለ(ፕ/ር) ናቸው።
በፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱም በአዲስ አበባ፣ አዳማ ደብረሲና እና የአዋሽ ከተሞች የደረሰ ነበርም ብለውናል።
በአዋሽ ፈንታሌ ባሳለፍነው አርብም የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበረም ነግረውናል።
መሬት በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ስላለች የመሬት መንቀጥቀጥ የሚከሰትበቀት ጊዜ በርግጠኝነት መናገር እንደሚቸግርም አስረድተዋል።
በተለይም የመሬት መንቀጥቀጥ በሚደጋገምባቸው አካባቢዎች ህንፃዎች ሲሰሩ መሰረታቸው እንዲጠናከሩም መክረዋል።
ወንድሙ ሀይሉ












Comments