top of page

ጥቅምት 13፣2017 - የኮንትሮባንድ ንግድ የቡና ጥራት እንዳላመጣ ችግር ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Oct 23, 2024
  • 1 min read

ከፋ፣ ቤንች ሸኮ አካባቢዎች ከፍተኛ ቡና አብቃይ ቢሆኑም፤ የኮንትሮባንድ ንግድ የቡና ጥራት እንዳላመጣ ችግር ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተናገረ፡፡


ክልሉ የቡና ቅመማ ቅመምና ሻይ ባለስልጣን፣ ይህን ለመከላከል ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የተዘረጋ ግብረ ሀይል አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስረድቷል፡፡


በክልሉ የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ አካባቢዎች ከፍተኛ #ቡና አብቃይ ሲሆኑ በተለይም ቤንች ሸኮ ከፍተኛ ቡና የሚመረትበት ስፍራ ነው፡፡


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቡና #ቅመማ _ቅመምና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበው የቡና ምርት ጥራቱ የጠበቀ እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡


ነገር ግን #ህገ_ወጥ_የቡና_ንግድ በክልሉ የቡና ጥራት ለማስጠበቅና የምርት መጠን በሚፈለገው ልክ እንዳይጨምር እንቅፋት ሆኗል ሲሉ ነግረውናል፡፡


ክልሉ በ2016 የምርት ዘመን 54,795 ቶን ቡና ፣ 53,900 ቶን ቅመማ ቅመም እና 6,654 ቶን የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ክልሉ ማቅረቡን ጠቅሰዋል፡፡


በ2017 የምርት ዘመንስ ምን ታቅዷል? በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ምን ያህል ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ተልኳል?



በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page