ጥር 24፣2016 - በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት መራዘሙ ተነገረ
- sheger1021fm
- Feb 2, 2024
- 1 min read
በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት መራዘሙ ተነገረ፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ዛሬ ውይይት አድርገውበታል ተበሏል፡፡
በዚህም ተጨማሪ ስራዎች በመኖራቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ 4 ወራት ማራዘም ማስፈለጉ ተነግሯል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጸደቀው በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ እንደሆነ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአማራ ክልል ለ6 ወር ታውጆ የነበረውና በመተገበር ላይ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጪው ማክሰኞ 6 ወሩን ይደፍናል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il












Comments