top of page

ጥር 2፣2016 - ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ለመስራት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራረሙ

11 ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ለመስራት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራረሙ።


ስምምነት የተፈራረሙት ባለሀብቶች በ5 የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ለመስራት ተስማምተዋል።


ባለሀብቶች በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በአልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ በመድሃኒት እና በፕላስቲክ ማምረት ላይ እንደሚሰማሩ ተነግሯል።


ወደ ስራ የሚገቡት ባለሀብቶች ከ100 ሚልየን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ያስመዘገቡ ናቸው የተባለ ሲሆን 31ሺ ካሬ ሜትር የማምረቻ ሼዶችን እና 4.5 ሄክታር የለማ መሬት መረከባቸውን ሰምተናል።


እነዚህ ባለሀብቶች ከ50,000 በላይ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር ይፈጥራሉም ተብሏል።


ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ውሰጥ ስራ ሲጀምሩ ለ 5,000 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራሉም ተብሏል።




ባለሀብቶቹ በመቀሌ፣ ጅማ፣ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ በእያንዳንዳቸው ሶስት፣ ሶስት የሚገቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በባህር ዳር እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ይገባሉ ተብሏል።


የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ አሁን ወደ ስራ የሚገቡት ባለሀብቶች ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ያቀርባሉ ብለዋል።


ኮርፖሬሽኑ በሰሜኑ ጦርነት ከስራ ውጪ የነበረው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ተነግሯል፡፡


በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



bottom of page