top of page

ግንቦት 8 2017 - ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ የታክስ ቅሬታ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • 8 minutes ago
  • 2 min read

ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ የታክስ ቅሬታ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተናገረ፡፡


ከእነዚህ መዝገቦች ገሚሶቹ ለመንግስት የተወሰኑ ገሚሶቹ ደግሞ ለቅሬታ አቅራቢዎቹ ተወሰኑ ናቸው ተብሏል፡፡


የግብር አከፋፈልና የጉምሩክ ጉዳዮችን በተመለከተ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የሚያቀርባቸው ቅሬታዎች በመመርመርና ሁለቱን በማከራከር በገለልተኝነት ፍትሃዊ ውሳኔዎችን እየሰጠ መሆኑን ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል፡፡


በዚህም ባለፉት 9 ወራት ከቀረቡለት 1ሺህ 144 የግብር አቤቱታ መዝገቦች ከ3.3ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ 686 መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው ተናግረዋል፡፡


ከዚህም ውስጥ 295 መዝገቦችን ለመንግስት አካላት ማለትም ለገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤትና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሲወስን 232 መዝገቦችን ደግሞ ለቅሬታ አቅራቢ ግለሰቦች መወሰኑንም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡


ሁለቱንም ወገን በማከራከር የመንግስት አካላትን ውሳኔ እስከ መሻር የደረሰ ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን አለንም ብለዋል፡፡


አንድ የግብር ቅሬታ በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውሳኔ ማግኘት አለበት የሚሉት የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ፤በኮሚሽኑ የገቢዎች ሚኒስቴርንና የጉምሩክ ኮሚሽንን ውሳኔ ሽረን ገንዘቡ ለቅሬታ አቅራቢው ተመላሽ እንዲሆን የአፈጻፀም መመሪያ ብንሰጥም፣ መስሪያ ቤቶቹ ሳይፈዕሙት ለረጅም ጊዜ ይቆያል፤ይህንን ችግር ለመፍታትና ይግባኝ ባዩ የተወሰነለትን እንዲያገኝ ለማድረግ እየተነጋገርን ነው ብለውናል፡፡


የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከየትኛውም የመንግስት አካላት ጋር ግንኙነት የሌለው ነው የተባለ ሲሆን በፌድራልና በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የቅሬታ ማቅረቢያ ቢሮዎች አሉት ተብሏል፡፡


የቅሬታ አቀራረብ ሂደቱም በተለይ የግብር ጉዳይ ከሆነ ቅሬታው በገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱ ቀርቦና ታይቶ ካልተፈታ ነው የሚሉት ሃላፊው፤ ወደ ኮሚሽኑ ሲቀርብ በኮሚሽኑ ችሎት ሁለቱንም ወገኖች በማከራከር ውሳኔ እንደሚሰጥም አብራርተዋል፡፡


የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስቴር የሆነ፤ የፕሬዝዳንቱና የዳኞች ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጥበት፤ የአሰራር መመሪያ የሚሰጠውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ ተቋም ነው፡፡


ይህ ከሆነ ታዲያ የገለልተኝነቱ ጉዳይስ ላልናቸው ፕሬዝዳንቱ ይህንን መልሰዋል፡፡


የኮሚሽኑን ውሳኔ እንዲያስፈፅሙ ቅሬታ ለቀረበባቸው ቢሮዎች ይላካል ተብሏል፤ ጉዳዩ ከኮሚሽኑ አልፎ ወደ ፍርድ ቤት የሚያመራው በውስጡ የህግ ስህተት ካለ ነው፤በዚህ ዓመትም 17 ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት እንደሄዱ ከሃላፊው ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page