top of page

ግንቦት 8 2017 - ኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶቿን ጨረታ ላይ ሲወጡ ጭምር እየገዛች ለማስመለስ ተገዳለች ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 24 minutes ago
  • 1 min read

ቅርሶች በህገ-ወጥ መንገድ ሲወጡ የኢትዮጵያ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ሰነድ ስለማይኖር ለማስመለስ ካሳ ትጠየቃለች ተብሏል፡፡


በዘረፋ መልክ በህገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ቅርሶች በኢንተርፖል ስለማይመዘገቡ አሁን ላይ እየተመለሱ ካሉ ቅርሶች መካከል ገንዘብ ተከፍሎባቸው የመጡ ይገኙበታልም ተብሏል።


አንዳንድ ሀገራት ቅርስን የማስመለስ ህጋቸው ጥብቅ በመሆኑ በሙዚየማቸው ያሉ ቅርሶችን ለማስመለስም አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ሰምተናል።


የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር የቦርድ ም/ ሰብሳቢ እና ብሔራዊ የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆኑት አሉላ ፓንክረስት ኢትዮጵያ በጦርነትም ሆነ በሌላ ምክንያት የተዘረፉትን ፣በግዥም ሆነ በስጦታ ከሀገር የወጡ ቅርሶቿን እያስመለሰች ቢሆንም በህገወጥ መንገድ ከሀገር የወጡ ቅርሶች በህጋዊ ባለቤትነት ማረጋገጫ መዝገብ ባለመስፈራቸው ቅርሶቹን ለማስመለስ ካሣ ለመክፈል እየተገደደች ነው ብለዋል፡፡


በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ግጭቶች ቅርሶች እየተዘረፉ መሆኑን ያነሱት አሉላ ፓንክረስት የተዘረፉትን በማስመለስ ስራ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር ያስፈልጋል ብለዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page