ግንቦት 6 2017 - ኢትዮጵያዊያን በውጭ ሀገራት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው ሲሰሩ፤ መብታቸው እንዲከበር ያስችላል የተባለን አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ኢትዮጵያ እንድትቀበል ተጠይቋል
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ኢትዮጵያዊያን በውጭ ሀገራት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው ሲሰሩ፤ መብታቸው እንዲከበር ያስችላል የተባለን አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ኢትዮጵያ እንድትቀበል ተጠይቋል።
ኮንቬንሽኑ በሀገር ቤትና በውጭ የቤት ሰራተኝነት ላይ የተሰማሩትን መብት ለማስከበር ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል ተብሏል፡፡
ይህን የጠየቀው በኢትዮጵያ በማህበራዊ ጉዳዮች እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየተገበረ የሚገኘው ሲቪኤም(CVM) የተሰኘው አለም አቀፉ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
በአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት ከተካተቱት ኮንቬንሽኖች መካከል ኢትዮጵያ ያፀደቀያቸው ቢኖሩም ኮንቬንሽን 189 የተሰኘውን ባለማፅደቋ በውጭ ሀገራትም ሆነ በሀገር ውስጥ ያሉ የቤት ሰራተኞች ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰቶች እንዲበራከቱ አድርጓል ተብሏል።
ይህ ኮንቬንሽን በተለየ መልኩ በቤት ሰራተኞች ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን የህግ ከለላ እንደሚሰጥም ተነግሯል።
ከዚህ ባለፈም ኮንቬንሽኑ የቤት ሰራተኞች የወሊድ ፈቃድ እንዲያገኙ፣ የጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል ይረዳል፣ አስፈላጊውን ደመወዝ እንዲከፈላቸውም ያስገድዳል ተብሏል።
የኮንቬንሽን 189 ሌላኛው ፋይዳ አሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲዎችን ጭምር ቁጥጥር እንዲደረግባቸው የሚያስገድድ መሆኑንም ሰምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
Comentarios