top of page

ግንቦት 5፣2017 - የነዳጅ ክፍያን በዳሽን ባንክ የሞባይል መተግበሪያ ወይንም "ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ "መክፈል ተጀመረ።

  • sheger1021fm
  • 22 hours ago
  • 1 min read


የዳሸን ባንክ ደንበኞቹ የነዳጅ ክፍያቸውን በቀላሉ የሚፈፅሙበትን ዲጂታል የክፍያ አማራጭ ማቅረቡን ባንኩ ተናግሯል።


ባንኩ ደንበኞቼ በተመረጡ የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ ሲቀዱ ክፍያቸውን በዳሸን ሱፐር አፕ በሶስት ክሊክ ብቻ መፈጸም ይችላሉ ብሏል።


በቅርቡም ዳሸን ባንክ ይህንን አገልግሎት በሁሉም ማደያዎች እጀምራለሁ ሲል አስረድቷል፡፡


የዳሸን ባንክ ደንበኞች የዳሸን ሱፐርአፕ መተግበሪያ ውስጥ በመግባት በሚኒ አፕ መተግበሪያ ውስጥ የሚገኘውን የነዳጅ ክፍያ (Fuel Payment) አማራጭ በመምረጥ የሚላክላቸውን የነዳጅ ክፍያ ኮድ በማስገባት ለገዙት ነዳጅ ከፍያቸውን መፈፀም ይችላሉ ተብሏል።


ወይንም ደግሞ በአማራጭነት የቀረበውን የኪው አር ኮድ ስካን በማድረግ በቀላሉ ክፍያቸውን ወዲያውኑ መፈፀም ይችላሉ ሲል ባንኩ አስረድቷል ፡፡


የነዳጅ ግብይቱን ለማዘመን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያበለጸገዉን የነዳጅ ስርጭት መከታተያ መተግበሪያ ከዳሸን ሱፐር አፕ ጋር በማጣጣም የነዳጅ ክፍያ መፈፅም እንዲያስችል ተደርጎ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡


ዳሸን ባንክ ከነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ጋር በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነም አስረድቷል፡፡


ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያ ነው ያለውን‘’ ሱፐር አፕ’’ ለአገልግሎት ወደ ስራ ማስገባቱን መናገሩ ይታወሳል።


የዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ የያዘ እና ዘመናዊ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑ ተጠቅሷል።


የነዳጅ ክፍያ አማራጩም በዚሁ መተግበሪያ ላይ መቅረቡ የተነገረ ሲሆን አጠቃቀሙም ቀላል ነው ተብሎለታል፡፡


ተህቦ ንጉሴ

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page