top of page

ግንቦት 26 2017 - ባለፉት 9 ወራት ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትና ከኃይል ስርቆት ጋር በተገናኘ ከ199 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Jun 3
  • 1 min read

ባለፉት 9 ወራት ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትና ከኃይል ስርቆት ጋር በተገናኘ ከ199 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ፡፡


በኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮች፣ ትራንስፎርመሮች፣ ኬብሎች ላይ በተፈፀመ ጉዳትና ስርቆት እንዲሁም ቆጣሪ በመነካካት፣ የኃይል ሰርቆት በመፈፀምና የተቋሙ ሰራተኞችን ስራ እንዳይሰሩ በማወክ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ላይ 199.5 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብ ጉዳት ድረሶብኛል ብሏል፡፡

ከዚህ ውስጥ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመ ጉዳትና ስርቆት ብቻ 52,33,123 ብር የሚገመት የገንዘብ ጉዳት ደርሷል ተብሏል፡፡


ይህንን ጥፋቱ ፈፀመዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ 208 የክስ መዝገቦችን መከፈታቸውንም አገልግሎtu ለሸገር ራዲዮ በላከው መግለጫ ተናግሯል፡፡


ከእነዚህም ውስጥ 27 መዝገቦች ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል የተባለ ሲሆን በዚህም ከ2 ወር እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደረስ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል ተብሏል፡፡


በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የተገዙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ መስመሮች ላይ ጉዳት፣ ውድመትና ስርቆት የሚፈፅሙ አንዲሁም የኢነርጂ ስርቆት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖች እየተበራከቱ መምጣታቸውንም ተጠቅሷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page