top of page

ግንቦት 22፣2017 - ዩኒቨርስቲዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ባለመሆናቸው ወደ ዩኒቨርስቲ ከሚገቡት መካከል 27 በመቶ በላዩ ትምህርታቸውን እንደሚያቋርጡ ጥናት አሳየ፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

ጥናቱን ያካሄደው የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር እንደሆነም ሰምተናል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች በምልክት ቋንቋ የሚያስተረጉምላቸው እንዲቀጥሩላቸው በመንግስት በኩል ጥያቄ ቢቀርብላቸውም በጀት የለንም በሚል አብዛኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሳይቀበሉት መቅረታቸውን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ጉጆ በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች በትምህርት ዘርፉ ላይ እንደሌሎች ሀገራት የተሻለ ትኩረት ስለማይሰጥ በርካቶች አካል ጉዳተኞች ከትምህርት እየተገለሉ ነው ብለዋል፡፡

ለአብነት በዩኒቨርስቲዎች የመሰረተ ልማት አለመሟላት ፣ የትምህርት ሥርዓት ተደራሽ አለመሆኑ እንዲሁም የመርጃ መሳሪያ አቅርቦት ውስን መሆን አካል ጉዳተኞች ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ማድረጉን ጥናቱ ያሳያል ብለዋል፡፡ አቶ አባይነህ መስማት ለተሳናቸው የምልክት ቋንቋ የሚችሉ አስተርጓሚ የቀጠሩ ዩኒቨርስቲዎች ካሉት ከ40 በላይ መካከል ከአምስት አይበልጡም ይላሉ፡፡

ይህም ዩኒቨርስቲዎች ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትኩረት አለመስጠታቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡

ፍቅሩ አምባቸው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page