top of page

ግንቦት 22፣2017 - የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል የተባለው ረቂቅ ህግ እውን የቤት ልማት ተደራሽን ያነቃቃል?

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

በየአመቱ ግማሽ ሚሊዮን የቤት ፍላጎት እያለ ግማሹን እምኳን ለማታሟላው ኢትዮጵያ ችግሩን ይፈታ ይሆን ?

የፋይናንስ ባለሙያዎች እንደሚሉት ረቂቅ ህጉ የውጭ ካፒታል እንዲገባ ያግዛል ቢባልም በሌላ መንገድ ገንዘብ ከኢትዮጵያ እንዲሸሽ ምክንያት ሊሆንም ይችላል፡፡

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፋይናንስ ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረዮሀንስ እንደሚሉት የውጭ ዜጎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያደርጋል የተባለው ህግ እንደተባለው የቤት ተደራሽነትን አያቀላጥፍም ወይም የቤት ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር እንዲመጣጠን አያግዝም ፡፡

ሲጀመር በጎረቤት ሃገራት እንኳን የቤት ግዥ ከኢትዮጵያ ሲነፃፀር ርካሽ ፣ ለውጭ ዜጎችም ቢሆን ከባንክ ጋር በማያያዝ በ20 እና 30 ሺህ ዶላር ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም የሚገኝ ነው ተብሏል፡፡

ረቂቅ ህጉ ግን የውጭ ሀገር ዜጎች በትንሹ 150 ሺህ ዶላር ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም የተከፈለ ካፒታል እንዲያቀረቡ የሚያስገድድ ነው፡፡


ይህም ኢትዮጵያን ለመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም አንፃር ተወዳዳሪም ፣ ተመራጭም አያደርጋትም፡፡

ታዲያ የውጭ ባለሀብቶች በየትኛው መስፈርት ኢትዮጵያን ይመርጧታል? ሲሉም ባለሙያው ይጠይቃሉ፡፡

ረቂቅ ህጉ የሌሎች ሃገራትን ተሞክሮም በማየት በአግባቡ እንዲፈተሽ አሳስበው የታመመው የኢትዮጰያ የመኖሪያ ቤት ገበያም በፖሊሲ ጭምር ማስተካከያ የሚያሻው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን

1 Comment


Vansh Sharma
Vansh Sharma
a day ago

A mere mention of the Escort in Dwarka is sufficient to tell you that it upholds topmost quality and great customer services. The agencies ensure that each client gets individual attention and a satisfying experience.


Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page