top of page

ግንቦት 21 2017 - በአፋርና ጋምቤላ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ዝግጁ መሆናቸው ተነገረ

  • sheger1021fm
  • May 29
  • 1 min read

በአፋር እና ጋምቤላ ክልል ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ፤ 400 ኪሎ ዋት አቅም ያላቸው የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተነገረ፡፡


ፕሮጀክቶቹ ከ 4,000 በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የፀሀይ ኃይል ማመንጫዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት የ25 የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነድፎ ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡


የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆኑት በአፋር ክልል ባዳ እና በጋምቤላ ክልል መተሃር በተሰኙ የገጠር ቀበሌዎች በግንባታ ላይ የነበሩ ሁለት የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል ተብሏል፡፡


የፀኃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ የግንባታ ስራ የተከናወነው ሲኢቲ ኤንድ ኤንአር ኮንሰርቲየም (CET and NR Consortium) በተባለ የቻይና ኩባንያ ሲሆን፤ የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ በድምሩ 400 ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸውም አገልግሎቱ ተናግሯል፡፡


ፕሮጀክቶቹ ከአዲስ አበባ በአማካይ 1,134 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በድምሩ 3.98 ኪሎ ሜትር የመካከለኛና 30.2 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር የተዘረጋላቸው እና 8 የተለያየ መጠን ያላቸው ትራንስፎርመሮችም ተገጥሟል ተብሏል፡፡


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





1 Comment


Tannu Rawat
Tannu Rawat
May 30

The majority of pleasure seekers search for stunning Escorts in Noida who will allow them to share some raucous times with those closest to them. At Noida Angecy, we guarantee that you will find companions who are unmatched in attractiveness.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page