ግንቦት 21 2017 15 - ''ሆቴሎች በዳግም ምዘናና ቁጥጥር ወቅት ዘርፍ መቀየራቸውን አረጋግጫለሁ'' የቱሪዝም ሚ/ር
- sheger1021fm
- May 29
- 1 min read
የቱሪዝም ሚንስቴር የ40 ሆቴሎች የዳግም ምዘና ውጤት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው ይህንን ያለው።
በዳግም ምዘና ወቅት ሸራተን አዲስ፣ ሀያት ሪጀንሲ፣ ስካይላይት፣ ካፒታል ሆቴልና ፓን ጨምሮ 11 ሆቴሎች ባለ 5 ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል።
ራዲሰን ብሉ፣ ኢሊሌ ኢንተርናሽናል፣ ማርዮት ኤክስኩይቲቭ፣ ጎልደን ቱሊፕ፣ ሂልተን አዲስ፣ ኢንተር ሌግዠሪና ኔክሰስ ሆቴል ሌሎቹ ባለ 5 ኮከብ ደረጃን ያገኙ ናቸው፡፡
ጁፒተር ኢንተርናሽናል፣ ሳፋየር አዲስ፣ ሀርመኒ ሆቴል ጨምሮ 9 ሆቴሎች ደግሞ ባል 4 ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል።
ነጋ ቦንገር፣ ሰሜን ሆቴል፣ አዲሲንያ ሆቴልን ጨምሮ 7 ሆቴሎች ባለ 3 ኮከብ ደረጃን ያገኙ ሲሆን 5 ሆቴሎች ደግሞ ባለ 2 ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል።
አዳዲስ አገልግሎት መሰጠት ከጀመሩ ሆቴሎች መካከል ስቴይ ኢዚ እና ቤስት ዌስተርን ፕርሚየር ሆቴል ባለ 4 ኮካብ ደረጃን አግኝተዋል።
መልካም አዲስ እና ጋራ ላይ ሆቴል ደግሞ ባለ 3 ኮከብ ደረጃን ያገኙ ሲሆን ቫይብስ እና ቦናንዛ ሆቴል ደግሞ ባለ 2 ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል ተብሏል።
በዚህ የኮከብነት ደረጃ ያልተደሰተ አካል ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል ሲሉ በቱሪዝም ሚንስቴር የቱዝም አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥና ደራጃ ምደባ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ታሪኩ ደምሴተናግርዋል።
ይህ የኮከብ ምደባ የሚያገለግለው ለመጪዎቹ 3 ዓመታት ብቻ መሆኑም ተነግሯል።
15 ሆቴሎች በዳግም ምዘና ቁጥጥር ወቅት ወደ ፔንሲዮንና ሌሎች ዘርፎች መቀየራቸውን አረጋግጫለሁ ሲል የቱሪዝም ሚንስቴር ተናገረ።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il












Everyone deserves to feel wanted and appreciated, especially during lonely or stressful times. Having someone who listens and understands can make a huge impact on your well-being. If you’re seeking warmth and connection, an Escort In Uttam Nagar might be the perfect match for you.