ግንቦት 20 2017 - የፌዴራል ተቋማትና ማህበራት ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ የሚያቀብሉበት መርሃ ግብር ከመጭው አርብ ጀምሮ ይካሄዳል
- sheger1021fm
- 2 days ago
- 1 min read
እንደ መከላከያ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፖሊስ ያሉ የፌዴራል የፀጥታ አካላት ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚኒስቴር መ/ቤቶችና ሌሎችም የፌዴራል ተቋማትና ማህበራት ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ የሚያቀብሉበት መርሃ ግብር ከመጭው አርብ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፌዴራሉ ተሳታፊዎች የሃገሪቱን ችግሮች ነቅሶ ከማውጣት ባሻገር መፍትሄ ያዘሉ ሀሳቦችንም ያቀብሉኛል ብዬም እጠብቃለሁ ብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለ3 ቀናት በሚካሄደው መርሃ ግብር ገዥው ፓርቲ ብልፅግናን ጨምሮ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ከሚሳተፉ አጀንዳ አቀባዮች መካከል ናቸው፡፡
በአጀንዳ ማሰባሰቡ ላይ እንደ አንድ ባለድርሻ የሚሳተፈው ብልፅግና ፓርቲም አሉኝ ያላቸውን አጀንዳዎች ይዞ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ ቀደም በፓርላማው ብልፅግና ፓርቲ የአስተዳደር ሥርዓቱን ከፓላሜንታዊ ወደ ፕሬዘዳንታዊ አስተዳደር ለመቀየር እየሰራ ነው ተብሎ ይታማል የሚል አስተያየት በቀረበ ወቅት የመንግስት ረዳት ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጅጌ(ዶ/ር) ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
በጉዳዩ ላይ ብልፅግና ካመነበት ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ እንዲደረግ ለሃገራዊ ምክክሩ እንደ አጀንዳ ሊያቀርበው እንደሚችል ፍንጭ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments