top of page

ግንቦት 20 2017 - ተሽከርካሪዎችን በየመንገድ ዳሩ እያስቆሙ ህግ ተላልፋቸዋል በማለት የቅጣት ወረቀት መስጠትና ቅጣት መጣል የከተማዋ ሰሞነኛ ምሬት ሆኗል፡፡

  • May 28, 2025
  • 1 min read

ተሽከርካሪዎችን በየመንገድ ዳሩ እያስቆሙ ህግ ተላልፋቸዋል በማለት የቅጣት ወረቀት መስጠትና ቅጣት መጣል የከተማዋ ሰሞነኛ ምሬት ሆኗል፡፡


አሽከርካሪዎች ከትንሹ አንድ ሺህ ብር ጀምሮ እስከ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር እና ከዚያም በላይ #የቅጣት_ገንዘብ እየተጣለባቸው መሆኑን ማየት ከጀመርን ዋል አደር ብለናል፡፡


አሽከርካሪዎችም ህግ አስከባሪ ትራፊኮች ሲያስቆሟቸው መደናገጥ አመላቸው ከሆነ ሰነባብቷል፡፡


በአጠቃላይ አሽከርካሪዎችን ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ይቆጥባቸዋል ተብሎ ተሻሽሎ የወጣው አዲሱ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ሾፌሮች አማሯቸዋል፡፡


የትራፊክ አደጋን ይቀንሳሉ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያስተካክላሉ ተብለው ከተከወኑ ስራዎች አንዱ አዲስ የተሻሻለው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ይገኝበታል፡፡


የትራፊክ እንቅስቃሴውን በሚገባ ይቆጣጠራል ለውጥ ያመጣል የተባለለት አዲስ የተሻሻለው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ከወራት በፊት ይፋ ሆኖ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡


ይሁንና በትራፊክ የመቆጣጠሪያ ደንብ ስር የተቀመጡ የቅጣት እርከኖች ላይ አሽከርካሪዎች ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይሰማል፡፡


ከወራት በፊት ተሻሽሎ ወደ ስራ የገባው አዲሱ የትራፊክ ደንብ የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴ እንጂ ለማስተማሪያነት የወጣ አይመስልም ሲሉ ቅሬታቸው ነግረውናል፡፡


በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ አሁን ያለው የመንገድ ሁኔታ አለመስተካከል የኑሮ ሁኔታ ሌሎች ነገሮችን ያላማከለ ሆኖብናል ያሉ ሲሆን ያሉትን ክፍተቶች መሰረት ያላደረገ እና ያላማከለ ቅጣት ነው ብለዋል፡፡


እኛም ከሾፌሮች የተነሱ ቅሬታዎች ይዘን ወደ አዲስ አበባ ትራፊክ ማናጅመት ባለስልጣን ጎራ ብለናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Recent Posts

See All
አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ማጠናከርና የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን አጠቃቀም ቁጥጥር ማጠናከር እንዲሁም የፋርማሲ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 22 2018 አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ማጠናከርና የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን አጠቃቀም ቁጥጥር ማጠናከር እንዲሁም የፋርማሲ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ። አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ኢትዮጵያ በመድኃኒት ምርት ራሷን መቻል እንዳለባት፣ በተ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page