top of page

ግንቦት 19 2017 - የገቢ ግብር እንዲቀንስ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ጥያቄው ሰሚ አላገኘምjust now

  • sheger1021fm
  • 23 hours ago
  • 2 min read

የተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢ ግብር እንዲቀንስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና በሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጭምር በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ጥያቄው ሰሚ አላገኘም፡፡


ሰራተኛም የሚከፍሉት የገቢ ግብር ከፍተኛ በመሆኑ ለነገ መቆጠብ እና ጥሪት መያዝ ቀርቶ በልተው ለማደር እንኳን መቸገራቸውን ያነጋገርናቸው ሰራተኞች ያስረዳሉ፡፡


ለመሆኑ መንግስት ለምን የሰራተኛውን #የገቢ_ግብር ቅነሳ ጥያቄ መመለስ አልፈለገም? የገቢ ግብሩ ቢስተካከል መንግስት የሚያጣው ምንድነው ? የጎረቤት ሀገራት ልምድስ እንዴት ያለ ነው?

ለመጠናቀቅ 40 ቀናት በቀረው በጀት ዓመት ወደ 900 ቢሊዮን ብር ከቀረጥ እና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ያለው መንግስት 50 ቢሊዮን ብሩን ከመንግስት እና ከግል ተቀጣሪ ሰራተኞች ለመሰብስብ እየሰራ መሆኑን የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት በለሙያው አቶ መርዕድ ፈቅረዮሃንስ ያስረዳሉ፡፡


አቶ መርዕድ መንግስት 50 ቢሊዮን ብሩን የሚሰበስበው ከግል እና ከመንግስት የጡረታ ፈንዶች እንደሆነ በመጠቆም በመንግስት 2.2 ቋሚ ተቀጣሪ እንዲሁም በግል በተመሳሳይ 2.2 ሚሊዮን በአጠቃላይ 4.4 ሚሊዮን ሰራተኞች አሉ የሚሰበሰበው 50 ቢሊዮን ብር ከእነዚህ ሰራተኞች ነው ይላሉ፡፡


የገቢ ግብሩ እርከን ቢስተካከል የ4.4 ሚሊዮን ሰራተኛውን ኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ባይችል እንኳን የተወሰነ አፎይታ ለሰራተኛው እንደሚሰጠው የሚያስረዱት ባለሙያው ከዛም ባለፈ አሰሪዎችም በነጻነት ሰራተኛ እንዲቀጥሩ ያበረታታል ይህም የስራ እድል ፈጠራን ያሳድጋል ባይ ናቸው፡፡


አቶ መርዕድ የጎረቤት አገራትን ተሞክሮ ሲስረዱም ኢትዮጵያ ሰራተኞች ዝቅተኛ ክፍያ እየተከፈላቸው ከፍተኛ ግብር ከፋዮች እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡


ለማሳያም #የኬንያን የሚነሱት ባለሙያው የሚቆርጡትን ግብር ከማየታችን በፊት የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ የኢትዮጵያና የኬኒያ የመገበያያ ገንዘብ ከዶላር አንፃር አቻ መሆናቸው ልብ ማለት ይገባል ይላሉ፡፡


ለማሳየም ከግብር አንፃር ስናይ ኬንያ 800 ሺህ ብር ከሚያገኝ ተቀጣሪ ላይ 35 በመቶ ግብር ስትቆርጥ ኢትዮጵያ ከ10 ሺህ 900 ብር ጀምሮ ተመሳሳይ ግብር ትቆርጣለች፡፡


እንዲሁም በኢትዮጵያ 600 ብር ከሚያገኝ ጀምሮ የገቢ ግብር ሲቆርጥበት በኬኒያ ግብር የሚቆረጠው 4 ሺህ ብር ከሚያገኝ ደሞዝኛ ጀምሮ ነው፡፡


የመግዛት አቅሙ ተዳክሞ ኪሱ የተራቆተው ሰራተኛ በመጠኑም እንዲያገግም መንግስት የሚቆርጥበት የገቢ ግብር ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ በተደጋጋሚ ተጠይቋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…….

ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page