top of page

ግንቦት 14 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • May 22
  • 2 min read

 

የዩክሬይን የቀድሞ ፕሬዘዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ልዩ ረዳት የነበሩት አንድሬይ ፖርትኖብ ስፔን ውስጥ ተተኩሶባቸው ተገደሉ፡፡

 

ፖርትኖቭ የተገደሉት በማድሪድ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ደጃፍ እንደሆነ አል ጀዚራ ፅፏል፡፡

 

ግለሰቡ ብዙ ጥይቶች ተተኩሰውባቸው እንደተገደሉ ተሰሟል፡፡

ree

ፖርትኖቭ ተተኩሶባቸው የተገደሉት ትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ወደነበረች መኪናቸው በሚገቡበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡

 

የጥቃት አድራሾቹ ማንነት ለጊዜው እንዳልተለየ ተጠቅሷል፡፡

 

የፖርትኖቭ ልጆች በተገደሉበት አቅራቢያ በሚገኘው ትምህርት ቤት እንደሚመሩ ታውቋል፡፡

 

የስፔን ፖሊስ ጉዳዩን መመርመር እንደጀመረ መረጃው አስታውሷል፡፡

 

 

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወደ ጋዛ ሰርጥ ሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ተማፀኑ፡፡

 

እስራኤል ከ2 ወራት በላይ ወደ ሰርጡ ሰብአዊ እርዳታ እንዳይገባ ከልክላ በመቆየቷ በጋዛ የሚኖሩ ፍልስጤማውያ ለረሃብ መጋለጣቸው ይነገራል፡፡

 

ሊዮ 14ኛ ወደ ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ የተማፀኑት በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተሰብስበው ለነበሩ 40 ሺህ የካቶሊክ ምዕመናን ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

ree

የጋዛው እልቂት እንዲያበቃም ጥሪ አቅርበዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፡፡

 

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ዳግም ወታደራዊ ዘመቻዋን ከጀመረች ከ2 ወራት በላይ ሆኗታል፡፡

 

ሊዮ 14ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ሳምንታዊ ንግግር ሲያደርጉ የትናንቱ የመጀመሪያቸው እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡

 

በአሁኑ ወቅት ወደ ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ መግባት መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

 

 

ካናዳም የአሜሪካውን የጎልደን ዶም የሚሳየል መከላከያ ውጥን ልትቀላቀል ነው ተባለ፡፡

 

የጎልደን ዶም የሚሳየል መከላከያ የወደፊቶቹን ዘመን አፈራሽ ሚሳየሎች ለመከላከል የተወጠነ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

 

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውጥኑን እወቁልኝ ያሉት ከትናንት በስቲያ ነው፡፡

 

ካናዳም የውጥኑ ተባባሪ የመሆን ፍላጎት እንዳላት ትራምፕ ተናግረዋል፡፡

 

የካናዳ መንግስትም በዚህ ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ንግግር መጀመሩን አረጋግጧል ተብሏል፡፡

 

የውጥኑ ማስጀመሪያ እስከ 25 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ተገምቷል፡፡

 

የጎልደን ዶም የሚሳየል መከላከያ ሥርዓት እንዴት እንደሚሰራ በዝርዝር የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

 

 

የአውሮፓ ህብረት በዌስት ባንክ የእስራኤል ወታደሮች በጉብኝት ላይ በነበሩ ዲፕሎማቶቹ ላይ ተኩስ መክፈታቸው በጭራሽ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው አለ፡፡

 

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደፃፈው የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ ጄኒን የሚገኘው የሰደተኞች ሰፈር ለመጎብኘት በመኪና በማምራት ላይ በነበሩ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማቶች አቅጣጫ ተኩስ ከፍተዋል፡፡

 

የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊዋ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር በጭራሽ ተቀባይነት የለውም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

 

የእስራኤል መንግስትም በዲፕሎማቶቹ አቅጣጫ ተኩስ የተከፈተበትን ሁኔታ አጣርቶ በአጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

 

የተለያዩ የአውሮፓ አገራት ሹሞችም መሰል መልዕክት ማስተላለፋቸው ታውቋል፡፡

 

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማቶች ላይ ተኩስ መከፈቱን በብርቱ አውግዞታል መባሉ ተሰምቷል፡፡

 

በዲፕሎማቶቹ አቅጣጫ ተኩስ ቢከፈትም በሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

 

የኔነህ ከበደ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page